ታንኮች የተሰጣት ዩክሬን አሁን ደግሞ ዐይኗን ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ላይ ጥላለች
ዩክሬን አራተኛው ትውልድ የተባሉ የውጊያ ጄቶች እንዲሰጣት እንደምትገፋፋ አስታውቃለች
አሜሪካና ጀርመን አብረሃምስና ሊዮፓርድ 2 የተባሉ ዘመናዊ ታንኮችን ለዩክሬን እንደሚጡ አስታውቀዋል
ከምእራባውያን ሀገራት ዘመናዊ የውጊያ ታንኮች የተበረከተላት ዩክሬን አይኗን ዘመናዊ የውጊያ ታንኮች ላይ መጣሏ ተሰምቷል።
ከኔቶ አጋር ሀገራት ዘመናዊ ታንኮች በእጇ እንደገቡ ያወቀችው ዩክሬን አሁን ደግሞ ዘመናዊ የዉጊያ ጄቶች እንዲሰጡኝ ግፊት አደርጋለሁ ብላለች።
አሜሪካ አብረሃስ ኤም 1 እንዲሁም ጀርመን ደግሞ ሊዮፓርድ 2 የተባሉ ዘመናዊ ታንኮችን ለዩክሬን እንደሚጡ በትናትናው እለት ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ጀርመን ከራሷ ክምችት 14 ታንኮችን ለዩክሬን ለመስጠት የወሰነች ሲሆን፥ በሶስት ወይም በአራት ወራት ውስጥ ኬቭ መሳሪያዎቹ እንደሚደርሷት ተነግሯል።
ይህንን ተከትሎም የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር አማካሩ ዩሪይ ሳክ፤ ቀጣይ ጉዟችን ተዋጊ ጄቶችን በእጃችን ማስገባት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
እና የመንፈልገው ኤፍ 16 ብቻ አይደለም 4ኛ ትውልድ የተባለው ዘመናዊ የውጊያ ጄቶችን ነው፤ ጄቶቹን በእጃችን ካስገባን ጦርነቱን የማሸነፍ እድላችን ሰፊ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በበኩላቸው፤ ለዩክሬን ተዋጊ ጄቶችን የምንሰጥበት ምንም አጋጢ የለመ፣ ሲሉ ተናግረዋል።
የሩሲያ የጸጥታ ምክርቤት ምክትል ሊቀመንበሩ ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ምዕራባውያን ለኬቭ የሚያደርጉት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ኒዩክሌር ጦርነት እንዳያስገባን ሲሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል።