ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው ሁሉንም ግዛቷን ነጻ ለማድረግ እንደሆነ መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹ
ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ለሰላም ሲባል መሬት አሳልፋ መስጠት ትፈልጋለች የሚለው ሀሰተኛ መረጃ ነው ብለዋል
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ከ34 ወራት በላይ አስቆጥራለች
ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው ሁሉንም ግዛቷን ነጻ ለማድረግ እንደሆነ መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹ።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ሩዝቴም ኡሜሮቭ በዛሬው እለት እንደገለጹት ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው ባለፈው አስር አመት በሩሲያ የተያዘባትን ግዛት ነጻ ለማድረግ ነው።
ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ለሰላም ሲባል መሬት አሳልፋ መስጠት ትፈልጋለች የሚለው ሀሰተኛ መረጃ ነው ብለዋል።
"ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅ የእሴታችን አካል ነው"ሲሉ ሚኒስትሩ ከኖርዋይ አቻቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ ተናግረዋል።
ዩክሬን ትኩረቷን ቀይራለች ስለሚሉት ሪፖርቶች የተጠየቁት ኡማሮቭ ይህ ሀሰት እና የሩሲያ ፕሮፖጋንዳ አካል ነው ሲሉ መልሰዋል።
"ትኩረታችን አሁንም ህዝባችንን መጠበቅ፣ ሀገሪቱን መጠበቅ፣ ህዝባችንን ከ10 አመት ጊዜያዊ ወረራ ነጻ ማውጣት ነው። ክሪሚያ እና ዶምባስ የዩክሬን አካል ናቸው" ብለዋል ኡሜሮቭ።
ኡሜሮቭ አክለውም እንደተናገሩት በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለው ግዛት የሚኖረው ህዝብ ነጻ ለመውጣት እየጠበቀ ነው።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ከ34 ወራት በላይ አስቆጥራለች።
ጦርነቱን በንግግር ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ሁለቱ ሀገራት ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እጅጉን የተራራቁ በመሆናቸው እስካሁን ጠብ የሚል ነገር አልመጣም።
ዩክሬን ጦርነቱ እንዲቆም የሩሲያን ከያዘቻቸው ግዛቶች ለቆ መወጣት በቅደመ ሁኔታነት ስታስቀምጥ፣ ሩሲያ ደግሞ ጦርነቱ የሚቅመው ኪቭ በእነዚህ ግዛቶች ላይ የይገባኛል ጥያቄዋን ስትተው ነው ብላለች።