በዩክሬን የሚሳዔል ጥቃት ቢያንስ 4 ሰዎች መሞታቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
ዩክሬን በሩሲያዋ ቤልግሮድ ከተማ ላይ በባላስቲክ ሚዔል ጥቃት መፈፀሟን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ፤ ዩክሬን የሩሲያ የድንበር ከተማ በሆነችው ቤልግሮድ ከተማ ላይ ቶችካ ዩ የተባሉ ሶስት የባላስተክ ም,ሚዔል ነው ያስወነጨፈችው።
ሩሲያ ሶስቱንም ሚሳዔሎች በአየር ላይ ያመነከች ቢሆንም የአንዱ ሚሳዔል ፍንጣሪ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቆ ጉዳት ማድረሱን አስታውቃለች።
በዚህም 11 አፓርትመንቶች እና 39 ጥቃቅን መኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት መድረሱ የተነገረ ሲሆን፤ በሰዎች ላይም ጉዳት ደርሷል።
የክልላዊ አስተዳዳሪ ቨያስቼስላቭ ግላድኮቭ እንደተናገሩት፤ በጥቃቱ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን እና አራት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል።
በጥቃቱ ከሞቱት ውስጥ ሶስቱ ዩክሬናውያን ሲሆኑ አንድ ደግሞ የሩሲያ ዜጋ መሆኑንም ገልፀዋል።
ዩክሬን በትናትናው እለት ቤላሩስ ላይም የሚሳዔል ጥቃት መሰንዘሯ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሌክሳነደር ሉካሽንኮ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ቤላሩስ የሚሳዔል ጥቃቱን “ፓንትሲር” በተባለ የአየር መከላከያ ስርዓት ተመትተው እንዲከሽፉ መደረጋቸውንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።