የዩክሬን ቀዳማዊ እመቤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጌጣጌጥ ማውጣታቸው ተገለጸ
ቀዳማዊ እመቤት ኦሌና ዘለንስካ ውድ ጌጣጌጦችን ገዝተዋል ተብሏል
በኒዮርክ ሊረዳቸው የነበረ የቡቲክ ሰራተኛም በዩክሬን ቀዳማዊ እመቤት ምክንያት ከስራ ተባሯል ተብሏል
የዩክሬን ቀዳማዊ እመቤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጌጣጌጥ ማውጣታቸው ተገለጸ።
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ በእርዳታ በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች።
ለተጨማሪ እርዳታ ፍለጋ እና በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኒዮርክ ያቀኑት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ባለቤታቸውም አብራቸው ተጉዛ ነበር።
ቀዳማዊ እመቤት ኦሌና ዘለንስኪም በኒዮርክ ወዳሉ ቅንጡ የጌጣጌጥ እና አልባሳት መሸጫ ሱቆች ጎራ ማለታቸው ተገልጿል።
አርማኒ፣ ጉሲካርቴር እና ሌሎችም ወደ ሚገኙባቸው የኒዮርክ ቅንጡ ቡቲኮች ያመሩት ኦሌና አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጋቸውን ዘ ኔሽን እና ቢኤንኤን ዘግበዋል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ቀዳማዊ እመቤቷን ለማስጎብኘት የፈለገ የአንድ ቅንጡ ቡቲክ ሰራተኛ "ተዳፍሯል" በሚል ለአለቃው ቅሬታ ማቅረቧን ተከትሎ ከስራ ተባሯል።
ይህንንም ተከትሎ ኦሌና ዘለንስካ የሀገር ሀብት በማካን ትችቶች የተሰነዘረባቸው ሲሆን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ትችቶችን አስተናግደዋል።
ከአንድ ዓመት በፊት ባለቤታቸው ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለዩክሬን ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚል ጋር ወደ ፓሪስ ባቀኑበት ወቅት 400 ሺህ ዩሮ ለቅንጡ እቃዎች ወጪ አድርገው ተመሳሳይ ትችቶች ደርሶባቸውም ነበር።