አሜሪካ ከኢራን በቁጥጥር ስር ያዋለችውን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ጥይት ለዩክሬን ሰጠች
አሜሪካ እስካሁን 200 ሚሊዮን ጥይቶችንና ፈንጅዎችን ለዩክሬን ሰጥታለች
ዋሽንግተን ከኢራን የወሰደችው ጥይት ሰኞ ዕለት በኪየቭ እጅ ገብቷል
አሜሪካ ባለፈው ዓመት ከኢራን የወሰደችውን 1.1 ሚሊዮን ጥይት ለዩክሬን መስጠቷን ተናገረች።
የዩክሬን ምዕራባዊያን አጋሮች የጥይት ማምረት አቅም ኪየቭ እየተጠቀመች ካለችው ጋር የመጣጣም ችግር እንዳለ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።
ዋሽንግተን እንዳስታወቀችው ከኢራን የተወሰደው ጥይት ሰኞ ዕለት በኪየቭ እጅ ገብቷል።
መካከለኛው ምስራቅን የሚከታተለው የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ፤ ጥይቶቹ ባለፈው ታህሳስ በየመን ከመርከብ ላይ እንደወረሰው አስታውቋል።
ጥይቱ የየትኛውንም ሀገር ሰንደቅዓላማ አልያዘችም ከተባለችው መርከብ በአሜሪካ ባህር ኃይል እንደተያዘ ተነግሯል።
ሀገሪቱ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ንብረቶች ከወንጀል እንቅስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ካላቸው መውረስን በሚፈቅደው አካሄዷ መሳሪያዎችን መረከቧም ተገልጿል።
የጥይት እርዳታው የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ለዩክሬን በሚያደርገው እርዳታ ተቃውሞ መግጠሙን ተከትሎ አማራጭ መንገዶችን እየፈለገ ባለበት ሰዓት የመጣ ነው።
አሜሪካ እስካሁን 200 ሚሊዮን ጥይቶችንና ፈንጅዎችን ለዩክሬን ሰጥታለች።
የዩክሬን የጥይት አቅርቦትን በሚመለከት በዋርሳው የጸጥታ ፎረም ኔቶ የመሳሪያ መጋዘኔ ባዶ ነው ብሏል።
ለአስርት ዓመታት የነበረው ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት የኔቶ አባል ሀገራት የጥይት ማከማቻ ግማሽ አሊያም ባዶ መሆኑንም ተናግሯል።