የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢራን ለሩሲያ የጦር መሳሪያ መስጠት እንድታቆም ኢራን ጠየቁ
የዩክሬን ፕረዝዳንት ሩሲያ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀምጥቃት እየፈጸመችብን ነው ማለታቸው ይታወሳል
ኢራን፤ ከዚህ በፊት ከሩሲያ የወሰድኩት የጦር መሳሪያ መለስኩ እንጅ በዚህ ጦርነት እጄ የለበተም ብላለች
ዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሩሲያ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም በመሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየፈጸመችብን ነው ሲሉ በቅርቡ ቴህራንን መክሰሳቸው የሚታወስ ነው፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ኪቭ ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ፍንዳታዎች መከሰታቸው አንስተው በሀገሪቱን ሲቪል ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ወደ 400 የሚጠጉ ኢራን-ሰራሽ ሻሄድ-136 ካሚካዜ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሰያ በኩል ጥቅም ላይ ውለዋል ሲሉም ከቀናት በፊት ተናግረው ነበር፡፡
ምንም እንኳን ቴህራን ለሩሲያ የሰጠሁት የጦር መሳሪያ የለም ሰትል ብትደመጥም፤ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ግን ቴህራን ለሞስኮ የጦር መሳሪያ መስጠት እንድታቆም የኢራን አቻቸው ሆሴን አሚራብዶላሂን መጠየቃቸው የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት "ዛሬ ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂን የስልክ ጥሪ ደረሰኝ እናም በዩክሬን ውስጥ ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል እና ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን ለማጥፋት ኢራን ወደ ሩሲያ የምትልከውን የጦር መሳሪያ በአስቸኳይ እንድታቆም ጠይቄያለሁ" ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚራብዶላሂን ቴህራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለሩሲያ ለዩክሬን ሸጥታለች በሚል ከዩክሬን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸው ሰኞ እለት መናገራቸው ዘ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ የዜና አገልግሎት ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ሚኒስትሩ ቴህራን ለሞስኮ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅርባለች የሚለውን የዩክሬን ክስም ውድቅ አድርገውታል፡፡
"ከዚህ በፊት ከሩሲያ የጦር መሳሪያ ወስደን የጦር መሳሪያም ሰጥተናል ነገር ግን በዩክሬን ጦርነት ጊዜ ያደረግነው ነገር የለም" ሲሉ መናገራቸውንም ነው ዘ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ የዜና አገልግሎት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጠቅሶ የዘገበው፡፡
ሚኒስትሩ በተጨማሪም ኢራን በዩክሬን ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ በሚደረገው ምርመራ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኗን ለአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል መናገራቸው አሰታውቋል፡፡
"ከኢራን እና ከዩክሬን የተውጣጡ ወታደራዊ ባለሙያዎች ቡድን በኢራን ሰራሽ ድሮኖች በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋሉን አስመልክቶ የቀረበውን የይገባኛል ጥያቄ ለመገምገም ዝግጁ መሆኔን ለጆሴፕ ቦሬል ነግሬቿዋለው"ም ብለውል ሚኒሰትሩ፡፡