ዩክሬን በቅርቡ የጠየቀችው የአሜሪካ መሳሪያዎች ምን አይነት ናቸው?
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች
ዩክሬን በቅርቡ ያቀረበችው የአሜሪካ መሳሪያዎች ዝርዝር፣ የሩሲያን ጦር ለመዋጋት ዘመናዊ የሆነውን የአየር መከላከያ ስርአት እንደምትፈልግ ጠቅሷል
ዩክሬን በቅርቡ የጠየቀችው የአሜሪካ መሳሪያዎች ምን አይነት ናቸው?
ዩክሬን በቅርቡ ያቀረበችው የአሜሪካ መሳሪያዎች ዝርዝር፣ የሩሲያን ጦር ለመዋጋት ዘመናዊ የሆነውን የአየር መከላከያ ስርአት እንደምትፈልግ ጠቅሷል።
እንደ ዶክመንቱ ከሆነ ዩክሬን ከአየር መከላከያ ስርአት በተጨማሪ ኤፍ-18 ተዋጊ ጀቶችን፣ ድሮኖችን፣ አፖች እና ብላክ ሃዋክ ሄሊኮፕተሮችን መታጠቅ ትፈልጋለች።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ባለስልጣናት በዋሽንግተን በተካሄደ ዝግ ስብሰባ የዩክሬንን የመከላከያ ኃይል ፍላጎት ያሟላል ያሉትን የመሳሪያ ዝርዝር ማቅረባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዩክሬን እንደምትፈልግ በዝርዝር ውስጥ ካካተተቻቸው መሰሪያዎች ውስጥ እንደ አብራም ታንክ እና 155 ሚሊሜትር አርቲለሪ የመሳሰሉት በክምችቷ ውስጥ ይገኛሉ።
ዩክሬን በሎክሂድ ማርቲን የተሰራውን ተርሚናል ሀይ አልቲቲዩድ አሪያ ዲፌንስ(THAAD) የተባለውን የአየር መከላከያ ስርአትም ጠይቃለች።
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከፍታ አወዛጋቢ ህዝበ ውሳኔ በማድረግ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ መጠቅለል ችላለች።
21 ወራትን ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እስካሁን ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል።