ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላትን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለማገድ የሚያስችል ህግ አጸደቀች
አብዛኛው ዩክሬን ህዝብ የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ቢሆንም እምነቱ ወደ ሁለት ቅርንጫፍ የተከፈለ ነው
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ እርምጃው የዩክሬናውያንን "መንፈሳዊ ነጻነት" የሚያጠናክር ነው ሲሉ አድንቀውታል
የዩክሬን ህግ አውጭዎች ከሩሲያ ጋር ግኝኑነት ያላት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ የሚያግድ ህግ አጽድቀዋል።
ይህ ኪቭ ከሞስኮ ጋር በመመሳጠር ከምትከሳት ቤተክርስቲያን ጋር ያላት ግንኙነት እንዲበጠሰ መንገድ የሚጠርግ እርምጃ ነው ተብሏል።
አብዛኛው ዩክሬን ህዝብ የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ቢሆንም እምነቱ ወደ ሁለት ቅርንጫፍ የተከፈለ ነው።አንደኛው ቅርጫፍ ከጥንት ጀምሮ ከሩሲያ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያለው የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ በአለም አርቶክስ አሰራር መሰረት እውቅና የተሰጠው ነጻ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነው።
የዩክሬን መሪዎች ከሞስኮ ግንኙነት ያላትን የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን እና 30 ወራት ያስቆጠረውን ጦርነት በማበረታት እና ሰላዮችን በማስጠጋት ይከሷታል።
በ265 ህግ አውጭዎች የጸደቀው ይህ ህግ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዩክሬን ግዛት እንዳይኖር ያግዳል፤ ከቤተክርስቲያኗ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶችም እንዲለዩ እና እንዲታገዱ ያዛል።
ዝርዝሩ በዋናነት የሚያካትተው የዩክሬን ኦርቶክስ ቤተክርስቲያን ተብሎ የሚጠራውን ቅርንጫፍ ነው።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ አመት እርምጃው የዩክሬናውያንን "መንፈሳዊ ነጻነት" የሚያጠናክር ነው ሲሉ አድንቀውታል።
ህግ አውጭ የሆኑት ኢርይና ሄራሽቸንኮ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ነበር ብለዋል።
"ይህ ታሪካዊ ምርጫ ነው። ፓርላማው በዩክሬን ያለውን የወራሪ ሀገር ቅርንጫፍ የሚያስወግድ ህግ አጽቋል" ሲሉ በቴሌግራም ገጻቸው ጽፈዋል።
ዩክሬን ኦርቶክስ ቤተክርስቲያን(ዩኦሲ) በታሪክ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አካል በትሆንም፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ወዲህ ራሷን ከሞስኮ ማራቅ ጀምራ ነበር።
ይሁን እንጂ የዩክሬን ባለስልጣናት በቤተክርስቲያኗ ላይ ጥርጣሪ ስላደረባቸው በደርዘን የሚቆጠር የወንጀል ምርመራ በማድረግ በአገልጋዮች ላይ የሀገር ክህደት ክስ ጭምር አቅርበዋል። ከተከሰሱት ውስጥ ቢያንሱ አንድ ሰው በእስረኛ ልውውጥ ወደ ሞስኮ ተልኳል።
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሜትሮፓሊታን የበላይ ጠባቂ ቤተክርስቲያኗ ከውጭ ማዕከላት ጋር ምንም ግንኘነት ገልጸው፣ህጉ ቤተክርስቲያኗን እና ንብረቷን ኢላማ ለማድረግ የወጣ ነው ሲሉ ተችተውታል።
" በአብኛው ዩክሬናውያን አማኞች በአለም አብያተ ቤተክርስቲያናት እውቅና ያላት የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ትቀጥላለች" ብለዋል።