አዲስ የሚወለዱ ዩክሬናዊን ህጻናት ቁጥርም ከዕጥፍ በላይ መቀነሱን ተመድ አስታውቋል
የዩክሬን ህዝብ ብዛት በ10 ሚሊዮን መቀነሱ ተገለጸ፡፡
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ከጠቅላላ ህዝቧ ውስጥ 10 ሚሊዮን ያህሉ እንደቀነሰ ተገልጿል፡፡
በመንግስታቱ ድርጅት የምስራቃዊ አውሮፓ እና ማዕከላዊ እስያ ዳይሬክተር የሆኑት ፍሎረንስ ባውር ተናግረዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ ዩክሬን ከጦርነቱ በፊት ዝቅተኛ የውልደት ምጣኔ የነበራት ቢሆንም በዚህ ልክ ግን የህዝብ ቁጠሯ መቀነሱ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከጦርነቱ በፊት በዩክሬን በአማካኝ አንድ ሴት ሁለት ህጻናትን ትወልዳለች ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይህ የውልደት ምጣኔ ወደ አንድ ቀንሷልም ተብሏል፡፡
ጦርነቱን በመሸሽ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ተለያዩ ሀገራት የተሰደዱ ሲሆን ቀሪው ህዝብ የት እንደገባ እስካሁን አልታወቀም፡፡
የሰሜን ኮሪያ ጦር ለሩሲያ ተሰልፎ በዩክሬን እየተወጋ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናገሩ
በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ምክንያት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዩክሬናዊያን ተገድለዋል ተብሎ ቢጠበቅም ቀሪ ዩክሬናዊን የት እንዳሉ ሊታወቅ እንዳልተቻለ አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን አልተሳኩም፡፡
ዩክሬን ጦርነቱን ስቆማል በሚል የድል እቅዷን ይፋ ያደረገች ቢሆንም እንደ አሜሪካ ካሉ አጋር ሀገራት በቂ ድጋፍ ማግኘት እንዳልቻለ ከሰሞኑ የተለያዩ ዘገባዎች ላይ ተጠቅሷል፡፡