ዩክሬን ባለፈው ወር ከ600 በላይ በሩሲያ ቁጥጥር ስር የነበሩ መንደሮችን ነጻ ማድረጓን ገለጸች
ነጻ ከወጡት መካከለ 7ቱ በኬርሶን የሚገኙ ናቸው ተብሏል
የተመድ ተጸጥታው ምክርቤትም ሩሲያ አራቱን የዩክሬን ግዛቶች ማጠቃለሏን አውግዟል
የዩክሬን የታጠቁ ሃይሎች ባለፈው ወር በጣም ስትራቴጂካዊ በሆነው ኬርሶን የሚገኙ 75 መንደሮን ጨምሮ ከ 600 በላይ ሰፈሮችን ከሩሲያ ስጋት ነፃ ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
የዩክሬን ጦር በሩሲያ ላይ ከባድ ጥቃት በመሰንዘር 502 ሰፈራዎች በሰሜናዊ ምስራቅ ካርኪቭ ክፍል በተሳካ ሁኔታ ነፃ መውጣታቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል።
ሚኒስቴሩ 43 ሰፈራዎች ወይም መንደሮችን በዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ግዛቶች ነፃ መሆናቸዉን ገልጿል።
"ነፃ የወጡ የዩክሬን ግዛቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል" ሲል ሚኒስቴሩ የድረ-ገጹን ግንኙነት በተሳካ ሁኔታ ገልጿል።
ሮይተርስ የጦር ሜዳ ሪፖርቶችን በተናጥል ማረጋገጥ አልቻለም፡፡
ሩሲያ ኬርሶንን፣ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ እና ዛፖሪዝዝሂያ ህወበ ውሳኔ በማካሄድ ወደ ግዛቷ ጠቅልላለች፤ በእነዚህ ግዛቶች ላይ የሚቃጣ ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ እንደሚቆጠር የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን መናራቸው ይታወሳል፡፡
ሩሲያን ድርጊት ዩክሬን እና ምእራባውያን ሀገራት በጽኑ ኮንነውታል፡፡
የተመድ ተጸጥታው ምክርቤትም ሩሲያ አራቱን የዩክሬን ግዛቶች ማጠቃለሏን አውግዟል፡፡
ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት የሞያደረገው መንቀሳቀስ እና የዩክሬን ወደ ኔቶ የጦር ህብረት እቀላቀላለሁ ማለቷ ስጋት ውስጥ የተከተታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለቸውን ወታደራዊ ዘመቻ ልትከፍት ችላለች፡፡ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት የሩሲያ ድርጊት አውግዘዋል፤ አለ የሚሉትን ማእቀብ ሁሉ ጥለውባታል፡፡