ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት ዩክሬን የኔቶ አባልነት ግብዣን እንደምትፈልግ ገለጸች
ዩክሬን የኔቶ አባል ከሆነች ከሩሲያ ጋር ዘላለማዊ ሰላም እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል
ኔቶ በበኩሉ የዩክሬን ጦርነት ባልቆመበት ሁኔታ በአባልነት እንደማይቀበል አስታውቋል
ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት ዩክሬን የኔቶ አባልነት ግብዣን እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡
ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አሁንም መቋጫ ያላገኘ ሲሆን ከሁለት ሳምንት ወር በኋላ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ዋነኛ መከራከሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡
በተለይም የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ጦርነትን በአንድ ቀን አስቆመዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ለዩክሬን ዋነኛውን ድጋፍ ያደረጉት እና ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ቀስ በቀስ ድጋፉን እየቀነሱ መጥተዋል፡፡
ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ የትኛውም እጩ ቢያሸንፍ ፕሬዝዳንት ባይደን የፊታችን ጥር ወር ላይ ስልጣን ማስረከባቸው አይቀሬ ሆኗል፡፡
ይህን ተከትሎ ዩክሬን ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት የኔቶ አባልነት ግብዣ እንዲቀርብላት ትፈልጋለች ተብሏል፡፡
በኔቶ የዩክሬን አምባሳደር ናታሊያ ጋሊባሬንኮ ለሮይተርስ እንዳሉት ሀገራቸው አሁን ላይ ከኔቶ የአባልነት ግብዣ እንዲቀርብላት ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
ብራዚል ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እንድታስር ዩክሬን ጠየቀች
አሁን ያለው የአሜሪካ አስተዳድር ለዩክሬን ድጋፍ በማድረግ ይታወቃል፣ ይህን ግኙነት ለማስቀጠል የኔቶ አባልነት ግብዣ እንዲቀርብ እንፈልጋለን ሲሉም አምባሳደሯ ተናግረዋል፡፡
ይሁንና አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎችም የኔቶ አባል ሀገራት ዩክሬን አሁን ባለችበት ሁኔታ የአባልነት ጥያቄ ማቅረብ እንደማይፈልጉ ተገልጿል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ማስቆም የሚስችል የሰላም እቅድ በሚል ካዘጋጁት ሰነድ ውስጥ ዩክሬን የኔቶ አባል እንድትሆን ማድረግ የሚለው ሀሳብ ተካቶበታል ተብሏል፡፡
ኔቶ በበኩሉ ዩክሬን የኔቶ አባል መሆኗ አይቀሬ ቢሆንም ወቅቱ ግን አሁን አይደለም ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡