የዩክሬኑ ጦርነት የአለም ኢኮኖሚ እድገትን በግማሽ ሊቀንሰው እንደሚችል የአለም ንግድ ድርጅት ገለጸ
የንግድ ድርጅቱ እንደገለጸው ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት ይልኩት የነበረው ምርትም ቀንሷል
የኔቶን ወደ ቀድሞ ሶቬት ሀገራት መስፋፋት የተቃወመችው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍታለች
በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት በዘንድሮው የፈረንቹ አመት የሚካሄደው ንግድ የአለም የንግድ ድርጅት (ደብሊው ቲ ኦ) በፈንጆቹ ባለፈው ጥቅምት ወር ከተነበየው 4.7 በመቶ እድገት በግማሽ በመቀነ ስ ወደ ከ2.4 እስከ 3 በመቶ ዝቅ ሊል ይችላል ብሏል፡፡
የግሎባል ሲሙሌሽን ሞዴል መጠቀሙን የገለጸው የንግድ ድርጅቱ ሴክሬታሪያት ጦርነቱ የአለም የምጣኔ ሀብት በ0.7 እስከ 1.3 በመቶ እድገት በመቀነስ ወደ 3.7 በመቶ ዝግ ሊደርገው ይችላል ብሏል፡፡
ጦርነቱ ሰብዓዊ ድቀትን ብቻ አይደለም ያስከተለው እንደ ድርጅቱ ሪፖርት፡፡ ይልቁንም የዓለምን የንግድ መጠን ተዛብቷል፤ የዓለም የንግድ ምጣኔ ከመቀነሱም በላይ ከፍተኛ የምግብና የነዳጅ ዋጋ ንረት ማጋጠሙን ገልጿል፡፡
የንግድ ድርጅቱ እንደገለጸው ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ተለያዩ ሃገራት ይልኩት የነበረው ምርትም ቀንሷል፤ ይህ በዋናነት ደሃ ሃገራትን ለከፋ ችግር የሚዳርግ ነው፡፡ ፖለቲካዊ መረጋጋትን ሊያሳጣቸውም ይችላል ብሏል ሪፖርቱ፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ግልጽ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን፤ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በሪፖርት ገልጿል።
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፣ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።
የዩክሬን ሃይሎች ጠንካራ ተቃውሟቸውን የፈጠሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሩሲያ ኃይሏን እንድታስወጣ ከፍተኛ ማዕቀብ ጥለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ውይይታቸውን ጀምረዋል።
የሩሲያ የፍትህ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን እና ሂውማን ራይትስ ዎች ጨምሮ የ15 የውጭ ድርጅቶችን ፍቃድ በመንጠቅ ቢሯቸውን ዘግቷል፡፡
ሩሲያ የድርጅቶቹን ፍቃድ የሰረዘችበትን ዝርዝር ምክንያት አለማቅረቧን ሮይተር ዘግቧል፡፡
የሩሲያ ፍትህ ሚኒስቴር ይህን ወሳኔ ያሳለፈው ዋና መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ የተሳተፉ ወታደሮቿ የጦርንትን ህግ በመጣስ መጠና ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥስት አካሂደዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡