ዩክሬን በአቭዲቪካ አቅራቢያ ያሉ ሁለት መንደሮችን ለቃ ወጣች
ዩክሬን ከአቭዲቪካ ለመውጣት የተገደደችው ወታደራዊ እርዳታ በቶሎ ባለመድረሱ ነው የሚል ምክንያት አቅርባለች
የዩክሬን ጦር በዚህ ወር መጀመሪያ በሩሲያ ከተያዘችው አቭዲቪካ አቅራቢያ ካሉ ሁለት መንደሮች ለቆ መውጣቱን አስታውቋል
ዩክሬን በአቭዲቪካ አቅራቢያ ያሉ ሁለት መንደሮችን ለቃ ወጣች።
የዩክሬን ጦር በዚህ ወር መጀመሪያ በሩሲያ ከተያዘችው አቭዲቪካ አቅራቢያ ካሉ ሁለት መንደሮች ለቆ መውጣቱን አስታውቋል።
አንድ ከፍተኛ አዛዥ እንደተናገሩት የዩክሬን ጦር በአቭዲቪካ ምስራቅ አቅጣጫ ለመከላከል የሚሆኑ ወታደራዊ ቦታዎችን እያጠናከረ ነው።
ኪቭ ላስቶቺካይ የተባለችውን መንደር ከለቀቀች ከአንድ ቀን በኋላ የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ ዲሚትሮ ላይኮቪ ከሲቨርን እና ስቴፕኦቭ ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።
"ሲቨሪን እና ስቴፕኦ ከተባሉ ሁለት ትናንሽ መንደሮች ኃይላችንን አስወጥተናል... በሲቨሪን በምሽት እና በሌሊት ከባድ ውጊያ ተካሊዷል" ያሉት ቃል አቀባዩ ሩሲያ ትልቅ ጉዳት አስተናግዳለች ሲሉም ተናግረዋል።
ቃል አቀባዪ እንዳሉት ዩክሬን ከሌሎች የምስራቅ ግንባሮች ጋር ትይዩ የሆነ ቦታዎችን ለመያዝ ወደ ኋላ አፈግፍጋለች።
ከጦርነቱ በፊት በሁለቱ መንደሮች 100 ሰዎች ይኖሩ ነበር።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሞስኮ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ከጀመረች ከሁለት አመት ከሶስት ቀናት በኋላ ሰቨሪን የተባለችውን መንደር መያዙን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የሩሲያ ጦር የተሻለ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች በመያዝ በስሶቱ መንደሮች አቅራቢያ የሚገኘውን የዩክሬን መሳሪያ እና የሰው ኃይል መምታቱን ገልጿል።
ሩሲያ አቭዲቪካን በመያዝ ባለፈው ግንቦት ባክሙትን ከያዘች ወዲህ ትልቅ ድል አስመዝግባለች።
የአቭዲቪካ መያዝ ትልቅ ስኬት ነው ያሉት ፑቲን የሩሲያ ጦር ተጨማሪ ቦታዎችን ለመያዝ ወደፊት እንደሚገፋ መናገራቸው ይታወሳል።
ዩክሬን ከአቭዲቪካ ለመወጣት የተገደደችው የምዕራባውያን ወታደራዊ እርዳታ በቶሎ ባለመድረሱ ነው የሚል ምክንያት ማቅረቧ ይታወሳል።
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና ከፍተኛ የዲሞክራት ፓርቲ አባላት ለዩክሬን 60 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እንዲለቀቅላት ግፊት እያደረጉ ነው ተብሏል።