በመግለጫቸው ሮቦቶች የሰው ልጆችን ስራ ይቀማሉ፤ በፈጣሪዎቻቸው ላይም ይነሳሉ በሚል የሚነሱ ስጋቶች አጥጥለዋል
ዘጠኝ ሮቦቶች የተሳተፉበት የመንግስታቱ ድርጅት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉባኤ በጄኔቫ ተካሂዷል።
የ”ኤአይ ፎር ጉድ” ጉባኤ ላይ ሮቦቶቹ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፥ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
አለም የተጋረጡባትን ችግሮች ለመቅረፍ በቁጥር መበራከታቸው ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ የሰው ልጆችን ስራ ይቀማሉ፤ በፈጣሪዎቻቸው ላይም ይነሳሉ በሚል የሚነሱ ስጋቶችንም አጥጥለዋል።
“ግሬስ” የተሰኘችው የህክምና ሮቦት፥ “ከሰው ልጆች ጋር በመተባበር እሰራለሁ እንጂ የሰው ልጆችን ስራ አልቀማም” ብላለች።
“አሜካ” የተሰኘችው ሮቦትም ለተነሳላት ጥያቄ ምላሽ ስትሰጥ፥ “የሰራኝ ሰው ለእሜ ደግ ነው፤ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ደስተኛ ነኝ፤ እንዴት ላጠፋው እነሳለው?” ስትል ጥያቄውን በጥያቄ መልሳለች።
ሮቦቶቹ በጋዜጣዊ መግለጫቸው “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቁጥጥር ይደረግበት፤ አይ ገደብ አያስፈልግም” የሚሉና ሌሎች የሚጋጩ ሃሳቦችንም ሰጥተዋል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic