ከ4.3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከዩክሬን ወደተለያዩ ሀገራት መጓጓዙን ተመድ ገለጸ
ከዩክሬን የተነሱት የእህል ምርቶቹ 29 ሀገራት መድረሳቸውን የተመድ ዋና ጸሃፊ ገለጹ
ጉቴሬስ፣ አሁንም የዓለም የምግብ ዋጋው አምና ከነበረበት በ8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቀዋል
ከ4.3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከዩክሬን ወደተለያዩ ሀገራት መጓጓዙን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የዓለም ነዳጅ እና ምግብ ዋጋ ለመናሩ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ይገለጻል።
የምግብ ዋጋን ለማረጋጋት እንዲቻልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እህልን በጥቁር ባህር በኩል ከዩክሬን ወደተለያዩ ሀገራት ለማጓጓዘ ከሩሲያ ጋር ስምምነት መደረሱ ጅታወሳል።
ስምምነቱን ተከትሎ የምግብ ተከትሎዋጋን ሊያረጋጉ ጥሩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ አስታውቀዋል።
ዋና ጸሃፊው በስምምነቱ መሰረት እስካሁን ከ4.3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከዩክሬን ወደ 29 ሀገራት መጓጓዙን አስታውቀዋል።
ይህንን ተከትሎ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በፍጥንት መቀነሱን ያስታወቁት ዋና ጸፋሂው፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ዋጋው አምና ከነበረበት በ8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቀዋል።
አሁንም ቢሆን የመርከብ ምልልሶች እና የሚጫነው የእህል መጠን መጨመር አለበት ያሉት ጉቴሬስ፣ ይህንን ማድረግ ከተቻለ የዓለም ገበያ የተረጋጋ ሊሆን እንደሚችል አክለው ገልጸዋል።
ዩክሬን የእህል ምርቷን ወደ አፍሪካ እና ወደ ሌሎች ሀገራት የምታስወጣበት የብላክ ሲ ወደብ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት መዘጋቱ በተለይም በአፍሪካ የምግብ እህል አቅርቦት እንዲያጋጥም አድርጎ ነበር፡፡
ተመድ ከቱርክ እና ከሩሲያ ጋር ባደረገው ስምምነት ምክንያት ሩሲያ በብላክ ሲ ላይ የጣለችውን ከበባ እንድታነሳ መስማማቷ ይታወሳል፡፡