በአፋር ክልል 5 ኤርትራውያን ስደተኞች ሲገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ከካምፓቸው ተፈናቀሉ
ተመድ ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው አልገለጸም
ተመድ የታጠቁ ኃይሎች በካምፑ ውስጥ የነበሩ በርካታ ሴቶችን ማገታቸውን ገልጿል
በአፋር ክልል ኤርትራውያን ስደተኞች በሰፈሩበት ካምፕ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ኤርትራውያን ሲገደሉ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተጠልለውበት ከነበረው ካምፕ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ገለጸ፡፡
የካቲት ስድስት 6፣2014.ም የታጠቁ ሃይሎች ወደ ካምፕ በመግባት የሰደተኞችን ንብረት እና ቤት መውረሳቸውን የተመድ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ወደ አፍር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ ተጉዘው የመጡ ስደተኞች እንደነገሩት ገልጿል፡፡
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ግጭት ከ20 ሺ በላይ ስደተኞች ከሰፈሩበት ካምፕ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ
- በኤርትራ ስደተኞች ላይ በሚደርሱ “የሰብአዊ መብት ጥሰቶች”ሪፖርት መጨነቁን ተመድ ገለጸ
ተመድ ከተፈናቀሉት ስደተኞች አገኘሁት ባለው መረጃ፣ በትንሹ አምስት ስደተኞች መገደላቸውን እና በርካታ ሴቶች መታገታቸውን ጠቅሷል፡፡ ከጥቃቱ ለማምለጥ በተፈጠረው ትርምስ የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው ተጠፋፍተዋል ብሏል፡፡
ተመድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በሰመራ ለሚገኙ 4ሺ ለሚሆኑ ስደተኞች የመጠለያ፣ የምግብና እና የውሃ አቅርቦት እያረሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ከሰመራ በ225 ኪ.ሜ ርቀት ላይ 10ሺ የሚሆኑ ስደተኞች አፍዴራ ከተማ እንደሚኖሩ የገለጸው ተመድ ቀሪዎቹ ደግሞ በአልፈፋ እና ዱባሬ መሰደዳቸውን ገልጿል፡፡
ተመድ እና አጋሮች ስደተኞችን በፍጥነት ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ እየተዘጋጃ ባለበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከሰመራ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የሰርዶ ከተማ ተመድና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ አዘጋጅቷል ብሏል ተመድ፡፡
በስደተኞች ካምፕ ላይ የተደረውን ጥቃት ማውገዙን የገለጸው ተመድ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ግጭቱ መቆም አለበት ብሏል፡፡
ተመድ ጥቃቱ መፈጸሙን ይግለጽ እንጅ የጥቃት አድራሾችን ማንነት አልገለጸም፡፡
የህወሃት ኃይሎች በሰሜን አፋር ክልል በሚገኘው ሰሜናዊ ዞን ዘልቀው በመግባት በርካታ ወራዳዎች መቆጣጠራቸውን እና አሁንም ጦርነት እንዳለ ክልሉ አስታውቆ ነበር፡፡ በጥቃቱ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን እና ከ300ሺ በላይ ንጹሃን መፈናቀላቸውን የአፍር ክልል መንግስት መግለጹ ይታወሳል፡፡
ህወሓት ቀደም ሲል ለሰላም እድል ለመስጠት ሲባል ከአፋር ክልል መወጣቱን ገልጾ ነበር፡፡