ጉቴሬዝ የሰሜነ ኢትዮጵያ ግጭት ከተጀረመረ ወዲህ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው ነው
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ #ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አክለውም “ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሐመትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።
“ትብብራችንን እንደሚጠናከር አልጠራጠርም” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጉቴሬዝ የሰሜነ ኢትዮጵያ ግጭት ከተጀረመረ ወዲህ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው ነው።