የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቤላሩስ የሚገኘውን የሀገሪቱን ኤምባሲ መዝጋቷን አስታወቀ
በጦርነት ውስጥ የሚገኙት ሩሲያ እና ዩክሬን በቤላሩስ በሚገኘው ጎሜል ግዛት ንግግር አድርገዋል፡፡
የሩሲያ ጎረቤት የሆነችው ቤላሩስ ሩሲያን ደግፋ ወደ ጦርነቱ መግባቷ ቢነገርም ቤላሩስ በጦርነቱ ውስጥ እንዳልገባች እና አስፈላጊ ከሆነ ግን እንደምትገባ ገልጻለች፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቤላሩስ የሚገኘው የአሜሪካ ሀገሪቱን ኤምባሲ መዝጋቷን አስታውቋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ ከሚገኙ ሰራተኞች መካከል ስራ ከሚበዛባቸው ውጭ ያሉት ሰራተኞች ለቀው እንዲወጡም አሜሪካ ጠይቃለች፡፡
ዋሸንግተን ውሳኔውን ያስተላለፈችው ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ባለው ጦርነት እንደሆነ ገልጻለች፡፡ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከገቡበት ከሃሙስ ዕለት ወዲህ አሜሪካ በሞስኮ ላይ በርካታ ማዕቀቦችን መጣሏ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የሩሲያ ሁነኛ አጋር ቤላሩስ ያለው ኤምባሲ እንዲዘጋ ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
አሜሪካ በቤላሩስ ያለው ኤምባሲዋ እንዲዘጋ የወሰነችው ቤላሩስ በጦርነቱ ላይ ወገንተኝነቷ ለሞስኮ ነው በሚል ነው፡፡ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በጦርነቱ ላይ ያላቸውን ሚና ምን እንደሆነ ተጠይቀው “እስካሁን በጦርነቱ አልተሳተፍንም ፤አስፈላጊ ከሆነ ግን እንሳተፋለን” ሲሉ መልሰው ነበር፡፡
ከሰሞኑ ጀምሮ አስተያየታቸው ይጠበቅ የነበረው ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ እየጣሏው ያሉ ማዕቀቦች “ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፋት ነው” ብለዋል፡፡ አሜሪካ በሚኒስክ ያለውን ኤምባሲዋን ከዘጋች በኋላ ከቤላሩስ የተሰማ አስተያየት የለም፡፡