የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር “ሩሲያ አስደናቂ የጦር መሳሪያዎች አሏት” አሉ
ሎለይድ ኦስቲን “የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ሞስኮ በዩክሬን ግጭት ውስጥ ድል እንድትቀዳጅ አላስቻላትም” ብለዋል
ሩሲያ በቅርቡ አሜሪካን ጨምሮ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ ነው ብላለች
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎለይድ ኦስቲን “ሩሲያ አስደናቂ የጦር መሳሪያዎች አሏት” ሲሉ ከሰሞኑ መናገራቸው ተሰምቷል።
መከላከያ ሚኒስትር ሎለይድ ኦስቲን ባሳለፍነው ቅዳሜ በካናዳ በተካሄደው የሃሊፋክስ ዓለም አቀፍ የፀጥታ መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራውም ስለ ሩሲያ ጦር ያነሱት የመከላከያ ሚኒስትሩ፤ የሩሲያ የጦር ኃሎች እና የጦር መሳሪያዎችን ማወደሳቸውን አር ቲ ዘግቧል።
መከላከያ ሚኒስትር ሎለይድ ኦስቲን በንግግራቸው “ታውቃላችሁ, ሩሲያውያን ግዙፍ ወታደራዊ አቅም እና አስደናቂ የጦር መሳሪያዎች አላት” ሲሉ ተናግረዋል።
ሆኖም ግን “ሩሲያ ያላት ወታደራዊ ኃይል እና የጦር መሳሪያ በዩክሬን ያደረገችውን ወረራ እንድታሸነፍ አልረዳትም” ስሉም የመከላከያ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ጦር አዛዥ ማርክ ሚሊ በቅርቡ ሰ,በሰጡት አስተያየት ዩክሬን በራሷ እና በምዕራባዊያን ሀገራት ድጋፍ በሩሲያ ላይ ድል እየተቀዳጀች መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል
ዩክሬን በሩሲያ ላይ ድል መቀዳጀቷ አይቀርም የሚሉት አዛዡ ይህ ድል ግን በቅርቡ ሊሆን አይችልም ሲሉም አክለዋል።
የአሜሪካ ጦር አዛዥ አክለውም፤ የሩሲያ ጦር አቅም አሁንም ከፍተኛ መሆኑን እና ዳግም ጥቃት ሊከፍት እንደሚችል መጠቆማቸውም አይዘነጋም።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመ ዘጠኝ ወራን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በዚህ ጦርነት ሩሲያ እንድትሸነፍ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በማስታጠቅ ላይ ናቸው።
ሩሲያ በበኩሏ ከወራት በፊት በመከላከያ ሚኒስቴሯ በኩል በሰጠየችው መግለጫ፤ ሩሲያ በዩክሬን ምድር ምዕራባውያን ጋር እየተዋጋች እንደሆነ መግለጿ ይታወሳል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሼጉ፤ ሀገራቸው በዩክሬን እያደረገች ባለው ጦርነት በተዘዋዋሪ ከምእራባውያን ጋር ውጊያ ላይ መሆኗ አሰታውቀዋል።
ሚንስትሩ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት በጦርነቱ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እያድረጉ እንሆነ አስታውቀዋል።