ኢትዮጵያ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ነበር
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ አራዘመች፡፡
አሜሪካ ከሶስት ዓመት በፊት የተቀሰቃሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይጎዳል በሚል ነበር ጦርነቱ እንዲቆም ጫና ስታደርግ የቆየችው፡፡
ይህ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገ የሰላም ስምምነት ቢቆምም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ግን እንደቀጠሉ ናቸው በሚል ማዕቀቡ ተራዝሟል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ምስራቅ አፍሪካን እና አሜሪካንን ይጎዳል በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡
በዋሸንግተን ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በኢትዮጵያ ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕቀብ የሚባል ሲሆን በፈረንጆቹ መስከረም 2021 ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ማዕቀብ ተጥሎ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህ ማዕቀብ ከአንድ ዓመት በፊት ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መፈረማቸው አይዘነጋም፡፡
ፕሬዝዳንቱ ፈርመውበት የነበረው ይህ ማዕቀብ ሊጠናቀቅ 10 ቀናት እየቀሩት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማለትም እስከ መስከረም 2025 ድረስ እንዲራም በፊርማቸው ማጽደቃቸውን ዋት ሀውስ በድረገጹ ላይ ይፋ አድርጓል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፈረሙበት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም አለመለወጡን ጉዳዩም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለምስራቅ አፍሪካ እና ለአሜሪካ የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ስጋት ነው ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ማይክ ሀማር ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው
የዓለማችን ባለግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው አሜሪካ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ ክስተት በየትኛውም ሀገር ሲከሰት ጥቅሟን ለማስከበር ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ትግበራ የተሰኘ ፖሊሲ ያላት ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በቀጥታ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ይፈቅዳል፡፡
ኢትዮጵያ እስካሁን በአሜሪካ አዲስ እርምጃ ዙሪያ ምላሽ ያልሰጠች ሲሆን የአሜሪካ የንግድ ችሮታ ወይም አግዋ እገዳ እንዲነሳ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኗን ከዚህ በፊት በተሰጡ መግለጫዎች ላይ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከማዕቀቡ በፊት በየዓመቱ ምርቶቿን ከቀረጽ ነጻ በሆነ መንገድ ወደ አሜሪካ ከተሞች በመላክ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት ላይ ነበረች።