ፖለቲካ
አሜሪካ በኒውክሌር ኃይል መስክ በዓለም ላይ ያላትን የበላይነት ማጣቷ ተገለጸ
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ አሜሪካ ከአሁን በኋላ በኑክሌር ኃይል ውስጥ መሪ አይደለችም ብሏል
ሩሲያ እና ቻይና በኒውክሌር ኃይል መስክ የመሪነት ስፍራውን መያዛቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል
አሜሪካ በኒውክሌር ኃይል መስክ በዓለም ላይ ያላትን የበላይነት ማጣቷን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ረፋኤል ገሮሲ፤ በሳለፍነው አርብ ዕለት በካርኔጊ በተካሄደው አለማቀፍ ሰላም ቲንክ ታንክ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር አድርገዋል
ረፋኤል ገሮሲ በንግግራቸውም አሜሪካ ከዚህ በኋላ በሲሊቪል የኒውክሌር ኃይል ዘርፍ የዓለም ቁንጩ አይደለችም ብለዋል።
አሜሪካ በኒውክሌር ኃይል ዘርፍ የነበራን የመሪበት ሚና በቻይና እና በሩሲያ መነጠቋን ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን አር.ቲ ዘግቧል።
አሜሪካ የመሪነት ስፍራውን መልሳ የመያዝ እድል ይኖራ ይሆን ተብለው የተጠየቁት ረፋኤል ገሮሲ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በንግድ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ውስጥ ከዚህ በኋላ እንደ ሩሲያ እና ቻይና መሆን አትችልም ብለዋል።