አሜሪካ ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቅርበት አላቸው ባለቻቸው ሩሲያውያን ቱጃሮች ላይ በድጋሚ እገዳ ጣለች
ሩሲያ ከድርጊቷ እስካልታቀበች ድረስ ማዕቀብ መጣሏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሜሪካ ገልጻለች
እገዳው ማንኛውንም የገንዘብም ሆነ የንብረት እንቅስቃሴ የሚመለከት ነው ተብሏል
አሜሪካ ለፑቲን ቅርብ ናቸው የተባሉትን የሩሲያ ቢልየነሮች ንብረት ማገዷ አስታወቀች፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የግምጃ ቤት የውጭ ሀብት ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት (OFAC) ዋቢ በማድረግ በድህረገጹ ሰፈረው መግለጫ እንደገለጸው ከሆነ በግለሰቦቹ ላይ የንብረት እገዳ የተጣለው አሁን ካለው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በተያያዘ ነው፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ኢ-ፍትሃዊ ጦርነት ማወጇን የሚትተው መግለጫው ፤ እገዳው ለቭላድሚር ፑቲን ቅርብ በሆኑና ኃብታቸው በአሜሪካ ውስጥ ያለ ወይም በአሜሪካ ውስጥ ባሉ ግለሰቦች እና አካላት የሚተዳደር ኃብትና ንብረት ባለቸው ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ነውም ብሏል፡፡
በተጨማሪም፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 50 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በአንድ ወይም በብዙ የታገዱ ሰዎች አክሲዮን ያለባቸው ንብረቶች ከሆኑ እንደሚታገዱ ተገልጿል፡፡
እነዚህ ክልከላዎች ማናቸውንም የገንዘብ፣ የእቃ ወይም የአገልግሎቶች አቅርቦት፣ ወይም የታገደ ሰው ማንኛውንም መዋጮ ወይም የገንዘብ አቅርቦት፣ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች መቀበልን ያካትታሉም ነው የተባለው።
እንደ የአሜሪካው የግምጃ ቤቱ የውጭ ሀብት ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት (OFAC) ከሆነ ንብረታቸው እና ኃብታቸው በልዩ ሁኔታ ከታገደባቸውና ለፑቲን ቅርብ ናቸው ከተባሉ አካላት እንደ ዩሪ ኮቫልቹክ፣ ኪሪል ኮቫልቹክ፣ ዲሜትሪ ሌባዴቭ፣ብላድሚር ኪንየግኒን፣ኢሌና ጎርጂቪያ የመሳሰሉትን ጨምሮ 13 የሩሲያ ቢልየነሮች ይገኙበታል፡፡
ፑቲን ከድርጊታቸው እስካልታቀቡ ድረስ አሜሪካ የሩሲያ መንግስት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ እንዲከፍል ላድረግ ቁርጠኛ እንደሆነችም አክሏል መግለጫው፡፡