አሜሪካ በሱዳን አለመረጋጋትን አባብሰዋል ባለቻችው አካላት ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች
ዋሽንግተን ግጭቱን ለግል ጥቅማቸው የሚያባብሱ አካላትን ኢላማ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብላለች
ማዕቀብ የተጣለባቸው አካላት የተኩስ አቁም እንዳይደረስ ማደናቀፋቸውን ተናግራለች
አሜሪካ በሱዳን አለመረጋጋትን አባብሰዋል ባለቻችው ሁለት ኩባንያዎች ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።
ዋሽንግተን ለሽህዎች ሞትና ለሚሊዮኖች ስደት ምክንያት ለሆነው ቀውስ ሩሲያ መቀመጫውን ያደረገ ኩባንያና አንድ ግለሰብ ላይ እግድ ጥላለች።
እርምጃው በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ጦርነቱ በሚያዚያ ወር ከፈነዳ ወዲህ ዋሽንግተን የወሰደችው አዲስ ዙር እቀባ ነው።
- የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በተመድ ስብሰባ እርስበእርሱ የሚቃረን መግለጫ ሰጡ
- የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ካርቱምን ዋና ከተማው አድርጎ መንግስት እመሰርታለሁ ሲል ዛተ
የአሜሪካ ግምጃ ቤት "የዛሬው እርምጃ በሱዳን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መፍትሄ እንዳይመጣ ያደረጉ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ ነው" ብሏል።
"ግጭቱን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚያባብሱ አካላትን ኢላማ ማድረጋችን ይቀጥላል" ሲልም አክሏል።
ግምጃ ቤቱ በኦማር አልበሽር ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በነበሩት አሊ ካራቲ ላይ እቀባ ማድረጉን አስታውቋል።
በተጨማሪም ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የመሳሪያ ግዢ ይፈጽማል የተባለ ጂኤስኬ ኩባንያም ማዕቀብ ተጥሎበታል።
"[ካርቲ] እና ሌሎች ጠንካራ የሱዳን እስላማዊ እንቅስቃሴ አራማጆች በጦሩና በፈጥኖ ደራሹ መካከል የተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት እና የሱዳንን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እያደናቀፉ ነው" ሲል ግምጃ ቤቱ ገልጿል።