ግጭት በሰላማዊ መንገድ የማስቆም፣ አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ በጂዳ ሁለቱንም ኃይሎች አገናኝተው የነበረ ቢሆንም ያለውጤት ተቋርጧል
አሜሪካ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎችን ለንግግር መጋበዟን ወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ።
አሜሪካ የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር በፈረንጆቹ ነሐሴ 14 በስዊዘርላንድ በሚካሄደው እና ራሷ በምትመራው የተኩስ አቁም ንግግር እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ተናገሩ።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ በዛሬው እለት ጠዋት "በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሰብአዊ እርዳታ ለተቸገሩ ሁሉ እንዲደርስ" ለማድረግ በንግግሩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ተናግረዋል።
"ጽኑ አቋማችንን በድጋሚ እናረጋግጣለን... ተጨማሪ ሰው እንዳይምት፣ ተኩሱ እንዲቆም እና ሀገሪቱ በሲቪል አስተዳደር እንድትመራ የሚያስችል ሰላማዊ እና በድርድር ላይ የተመሰረት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ እንፈልጋለን " ብለዋል።
በንግግሩ የአፍሪካ ህብረት፣ አረብ ኢምሬትስ እና ተመድ በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ብሊንከን በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል። ሳኡዲ አረቢያን ከአሜሪካ ጋር በጋራ በመሆን ንግግሩን እንደምትመራ ብሊንከን አክለው ገልጸዋል።
"በሱዳን የደረሰው የሞቱ መጠኑ፣ ስቃዩ እና ውድመት አስከፊ ነው። ይህ ትልጉም የለሽ ግጭት መቆም አለበት" ያሉት ብሊንከን የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር በንግግሩ ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በፈረንጆቹ ሚያዝያ አጋማሽ 2023 የተጀመረው የሱዳን ጦርነት 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንዲፈናቁሉ እና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግድያዎች እንዲቀሳቀሱ ምክንያት ሆኗል።
በተለይም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር በምዕራብ ዳርፉር የብሔር ጥቃት ፈጽሟል የሚል ክስ ይቀርብበታል። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ይህን ክስ አይቀበሉትም።
አሜሪካ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድሜዳሜ ላይ መድረሷን ማሳወቋ ይታወሳል።
የሱዳኑን ግጭት በሰላማዊ መንገድ የማስቆም፣ አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ በጂዳ ሁለቱንም ኃይሎች አገናኝተው የነበረ ቢሆንም ያለውጤት ተቋርጧል።