አሜሪካ ብቻዋን እስካሁን ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው የጦር መሳሪያና ሌሎች ድጋፎችን ሰጥታለች
የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ክምችት መመናመኑ ተገለጸ።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ዘጠኝ ወራት ሆኗታል።
ይህ ጦርነት በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ሲሆን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ፣ ገንዘብ፣ ወታደራዊ መረጃዎች እና ሌሎች ድጋፎችንም በማድረግ ላይ ናቸው።
- አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ የ11 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች
- ጆ ባይደን፤ አሜሪካ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለዩክሬን እንደምትሰጥ አስታወቁ
አሜሪካ ብቻዋን እስካሁን ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው የጦር መሳሪያ፣ የቀጥታ ገንዘብ እና ሌሎች ድጋችን ሰጥታለች።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ለዩክሬን ለመስጠት ማቀዳቸው ሲገለጽ የሀገሪቱ የጦር ማሰሪያ ክምችት መመናመኑን ሲኤንኤን ዘግቧል።
በተለይም ሩሲያ እንደ አዲስ የአየር ላይ ጥቃቶችን ማስፋፋቷን ተከትሎ ዩክሬን አሜሪካ የጸረ አየር ላይ ጥቃት መከላከያ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰጧት መጠየቋ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ላይ ጫና እንደፈጠረ ተገልጿል።
በዚህም ምክንያት አሜሪካ ተጨማሪ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች እንዲመረቱ ማድረጓ አሳሳቢ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህም ዋሸንግተን ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ቀጥታ ጦርነት ውስጥ ሳትሆን ይህ የጦር መሳሪያ ክምችት ሊመናመን ችሏል ተብሏል።
ይህ የጦር መሳሪያ ክምችት የፔንታጎን ባለስልጣናትን እና ባለሙያዎችን ወደ ክርክር እንዲገቡ ማድረጉ ሲገለጽ በቀጣይ ለዩክሬን የሚደረጉ የጦር መሳሪያዎች ይሄንን ግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ ሊሆን ይገባል መባሉን ዘገባው አክሏል።
ይሄንንም ተከትሎ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሊዮልድ ኦስቲን እና የአሜሪካ ጦር ዋና አዛዥ ማርክ ሚሌይ የአሜሪካንን የጦር መሳሪያ ክምችት መጠን እና የጦር እቅድን እየገመገሙ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለም ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምክር ቤት ምርጫ ለይ አብላጫ ወንበሮችን የተቆጣጠሩት ሪፐብሊካን ፓርቲ ተመራጮች የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ለዩክሬን የሰጠው ድጋፍ ኦዲት እንዲደረግ በመጠየቅ ለይ ናቸው።