የአሜሪካና የሩሲያ ባለስልጣናት በመጀመሪያው የሪያድስብሰባቸው በም ጉዳዮች ላይ ተስማሙ?
የሳዑዲው ምክክር ላይ ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካና የሩሲያን ግንኙነት ማሻሻል ላይም ይመክራሉ

በስብሰባው ላይ አንድም የዩክሬን ባለስልጣን አልተሳተፈም ተብሏል
የአሜሪካና የሩሲያ ባለስልጣናት የዩክሬን ጦርነትን ማስቆም በሚቻልበት ዙሪያ ለመምከር በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ተገናኝተዋል።
በሪያዱ ምክክር የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የመሩት ልኡክ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭና ከቭላድሚር ፑቲን አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ፊት ለፊት ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።
የሁለትዮሽ ምክክሩ የዋሽንግተን እና ሞስኮን ግንኙነት ማሻሻል በሚያስችሉ እና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም በሚያግዙ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ተነግሯል።
በውይይታቸውመ መጨረሻ የሩሲያና የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በሪያድ ስብሰባቸው፤ የዩክሬኑ ጦርነት እንዲያበቃ የሚደራደር የባለሥልጣናት ቡድን ለመሰየም ተስማተዋል
የአሜሪካ የሩሲያ አሜሪካና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማሻሻል ከስምምነት መድረሳቸውም ታውቋል።
በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ በተካሄደው በስብሰባ ላይ አንድም የዩክሬን ባለስልጣን አልተሳተፈም ተብሏል።
ዩክሬን እና የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬን ያልተሳተፈችበት የሰላም ንግግር የሶስት አመቱን ጦርነት አያስቆምም፤ ውጤቱም ተቀባይነት አይኖረውም እያሉ ነው።
ዩክሬን በስብሰባው ላይ አለመጋበዟን ተከትሎ ቀድም ብላ በሰጠች መግለጫ፤ ዩክሬን በራሷ ጉዳይ ባልተጋበዘችበት ድርድር የሚደረስ ስምምነትን አትቀበልም" ብላለች።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ኬቭ በሪያዱ የአሜሪካ እና ሩሲያ ድርድር ዙሪያ "የምታውቀው የላትም" ብለዋል።
"ዩክሬን በራሷ ጉዳይ ባልተጋበዘችበት ድርድር የሚደረስ ስምምነትን አትቀበልም" ሲሉም አብራርተዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ኬቭ በሞስኮ የተያዙባት ግዛቶችን መልሳ እንደማታገኝ እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባልነት ጥያቄዋ እንዲቆም የሚሰጡት አስተያየት ዜለንስኪ እና የአውሮፓ መሪዎችን አስቆጥቷል።