ጦርነቱ ካልቆመ በኢትጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደምትጥልም አሜሪካ አስጠንቅቃለች
አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በአራት ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል።
ማዕቀቡ ከተጣለባቸው ግለሰቦች መካከል አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ ህዝብ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ንቅናቄ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ሀጎስ ገብረህይወት ናቸው።
በተጨማሪም የኤርትራ መካላከያ ሰራዊት እና የኤርትራው ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትሕ (ህግደፍ) ማዕቀብ እንተጣለባቸው የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል
የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ነብረት የሆነው ህድሪ ትረስት እና የቀይ ባሕር ንግድ ኮርፖሬሽንም ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቋማት መሆናቸውም ታውቋል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቀዋማት እና ግለሰቦች በአሜሪካ ያላቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እና የጉዞ እገዳን ያካትታል።
ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በትግራይ ክልል በንጹሃን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽማዋል በሚል መሆኑንም ግምጃ ቤቱ አስታውቋል።
ጦርነቱ ቆሞ ሁሉም የጦርነቱ ተሳታ አካላት ወደ ተኩስ አቁም እና ድርድር እንዲመጡም አሳስቧል።
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከቀጠለ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች እንደሚጣሉም ተገልጿል።
አሜሪካ ከዚሁ ከትግራይ ክልለ ጋር በተያያዘ በኤርትራ ጦር ዋና አዛዥ በጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።