ዘለንስኪ ስልጣን ለመልቀቅ ያስቀመጧቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ሾሊድሚር ዘለንስኪ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

ዘለንስኪ ስልጣን ለመልቀቅ የዩክሬንን ሰላም ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ሾሊድሚር ዘለንስኪ "ስልጣኔን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ" ሲሉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ሾሊድሚር ዘለንስኪ ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ ላይ የሚያስቀምጧቸው ቅምድ ሁኔታዎች የሚሟሉ ከሆነ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት።
ዘለንስኪ ስልጣን ለመልቀቅ የዩክሬንን ሰላም ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል ነው የተባለው።
በዚህም ዘለንስኪ የእኔ ስልጣን መልቀቅ ለዩክሬን ሰላ የሚያመጣ ከሆነ ይህን ለማድረግ የሚያግደኝ የለም ብለዋል።
የኔቶ አባልነትንም እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት ዘለንስኪ፤ “ከስልጣን መነሳቴን በዩክሬን የኔቶ አባልነት መለወጥ እፈልጋለሁ" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ትኩረቴ የዩክሬን ሰላምና ደህንነት እንጂ የሚቀጥሉት 20 ዓመታት አይደለም” ያሉት ዘለንስኪ፤ “እኔም በስልጣን ላይ ለአስርት ዓመታት የመቆየት ፍላጎቱም የለኝም” ብለዋል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በቅርቡ በአሜሪካው አቻቸው ከስልጣን ጋር በተያያዝ ትችት እንደቀረበባው ይታወሳል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ዘለንስኪ ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው" ማታው ይታወሳል።
በትራምፕ ንግግር ዙሪያ የተጠየቁት ዘለንስኪ፤ “በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ማድረግ ባለችልም፤ ንግግሩን ግን እንደ አድናቆት አልመለከተው” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት አለንስኪ አክለውም “እኛ ከአሜሪካ ጋር አጋሮች ነን ከጎናችን እንዲሆኑ እንፈልጋለን” ብለዋል።