አሜሪካ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ተላልፈው እንዲጡ ወሰነች
የአሜሪከ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የታገዱ የሩሲያያ ንብረቶች ለዩክሬን እንዲሰጡ የመጀመሪያ ውሳኔ አሳልፈዋል
ሩሲያ ንብረቶቿን አሳልፎ መስጠት ሌላ መዘዝ ያስከትላል በማለት ማስጠንቀቋ ይታወሳል
አሜሪካ ከሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ የታደጉ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ተላልፈው እንዲሰጡ መወሰኗ ተገለፀ።
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ ጦርነት ከተጀመረ 15 ወራት ተቆጥረዋል። ይህ ጦርነት በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች እንዲጣሉባት አድርጓል።
አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት ከማዕቀቡ ባለፈ የሩሲያ መንግስት እና ባለሀብቶች ንብረት የሆኑ ሁሉንም ሀብቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያገዱ ሲሆን ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሩሲያዊያንን ገንዘብ ጥቅም ለማዋል ማቀዳቸው ተገልጿል።
በተለይም የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ የታገዱ የያሩሲዊያን መንግስት እና ዜጎች ሀብትን ለዩክሬን መልሶ ግንባታ እንዲውል እያሰቡ መሆኑን መግለጻቸውም ይታወሳል።
የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ የታገዱ የያሩሲያ መንግስት እና ዜጎች ሀብትቶች ለዩክሬን ተላለፈው እንዲሰጡ የመጀመሪያውን ውሳኔ አሳልፈዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ትናንተ በሰጡት መግለጫ፤ ከሩሲያው የተያዙ ገንዘቦች በጦርነት ለተጎዳች ዩክሬን ይሰጣሉ ሲሉ አስታውቃዋል።
ለዩክሬን ተላለፎ የሚሰጠው ገንዘብም ከሩሲያዊው ባለሀብት ኮስታሊን ማሎፌቭ የተወረሰ እንደሆነም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል።
ይህ አሜሪካ ከተያዙ የሩሲያ ንብረቶች ውስጥ ለዩክሬን አስተላልፋ የሰጠችው የመጀመሪው ነው እንጂ የመጨረሻው አይደለም ያሉ ሲሆን፤ የሩሲያን ንብረቶች ለዩክሬን አስተላለፎ መስጠቱ ይቀጥላልመ ብለዋል።
ሩሲያ ከዚ ቀደም በሰጠችው መግለጫ፤ እንዳይንቀሳቀሱ እገድ የተላለፈባቸው የሩሲያዊያን ሀብትን ለዩክሬን መስጠት የሚያስችል ዓለም አቀፍ ህግ እንደሌለ መግለጿ ይታወሳል።
ድርጊቱ ሌላ ዓለም አቀፍ መዘዝ ያስከትላል ስትል በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃም ነበር።