ፖለቲካ
አሜሪካ በሩሲያዋ ሞስኮ 'በአክራሪዎች' የማይቀር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ስትል አስጠነቀቀች
ሩሲያ ከአፍጋኒስታን እስላማዊ ታጣቂ ሊሰነዘር የታቀደ ተኩስ ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል
በሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲ የአሜሪካ ዜጎች በአፋጣኝ ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል
በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሞስኮ 'በአክራሪዎች' የማይቀር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ሲል ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫውን ያወጣው የሩሲያ የፀጥታ አካላት በሞስኮ ከአፍጋኒስታን እስላማዊ ታጣቂ ሊሰነዘር የታቀደ ተኩስ እንዳከሸፈ ማሳወቁን ተከትሎ ነው።
ሆኖም ግን በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አካራሪዎች በሩሲያ የማይቀር የጥቃት የመፈጸም እቅድ አላቸው ብሏል።
የአሜሪካ ዜጎች በቀጣይ 48 ሰዓታት ውስጥ ሰዎች በብዛት ወደሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ከመሄድ እንዲቆጠቡና አካባቢያቸውን እንዲያጤኑ አሳስቧል።
ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ላቲቪያ ጨምሮ የአሜሪካ አጋሮች የዩናትድ ስቴትን ማስጠንቀቂያ በመድገም ዜጎቻቸው ወደ ሩሲያ እንዳይጓዙ አሳስበዋል ነው የተባለው።
አብዛኞቹ ምእራባውያን ሀገራት ዜጎቻቸው ሩሲያ እንዳይጓዙ የሚመክሩ ሲሆን፤ ዜጎቻቸው በአፋጣኝ ሞስኮን ለቀው እንዲወጡም ያሳስባሉ።
አሜሪካ ለሩሲያ ከፍተኛውን የጉዞ ክልከላ የማስጠንቀቂያ ደረጃ ያወጣች ሲሆን፤ ደረጃውም “ቀይ 4” መሆኑን እና ከአፍጋኒስታን፣ ሶሪያ፣ የመን፣ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ኢራን ጋር ተመሳሳይ ነው።