ፖለቲካ
ዋግነር ግሩኘ ህልውናውን ሊያከስም እንደሚችል ገለጸ
ዋግነር ከዚህ በፊት በሶሪያ እና ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ወታደሮቹን በመላክ በጦርነት መሳተፉ ይገለጻል
አሜሪካ ባለፈው ጥር ይህን ቡድን ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ድርጅት በሚል ፈርጃዋለች
በዩክሬን በባክሙት ግንባር ጦርነቱን እየመራ ያለው የሩሲያው የግል ሚሊሻ ወይም ዋግነር ግሩፕ በቅርቡ ህልውናውን ሊያከስም እንደሚችል መስራቹ የቨግኒ ፕሪጎዚን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዋግነር ግሩኘ ከዩክሬን በተጨማሪም በአፍሪካ እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። ነገርግን ፕሪጎዚኒ ይህን መቼ እንደተናገሩ እና ምን ያህል ከልባቸው እንደሆነ አለመታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሪጎዚኒ በቅርቡ በዩክሬን ስላለው ሁኔታ የጻፉትን ማንሳታቸው ተገልጿል። ፕሪጎዝኒ ሩሲያ በዩክሬን በምታካሂደው ጦርነት ላይ በተደጋጋሚ ቅሬታ በማቅረብ የሚታወሱ ናቸው።
የሩሲያው መደበኛ ጦር በቂ ተተኳሽ እየሰጠን አይደለም የሚል ቅሬታ ነበር ብዙ ጊዜ እንደቅሬታ የሚያቀርቡት።
ኘሪጓዚኒ ይህንን ድርጊት ክህደት ሲሉ ይገልጹታል።
"ዛሬ ዋግነር ህልውናው ማብቃት ወደሚል ነጥብ ደርሰናል" ሲሉ ለሩሲያው የጦርነት ብሎገርሰምዮን ፔጅጎቭ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዋግነር ከዚህ በፊት በሶሪያ እና ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ወታደሮቹን በመላክ በጦርነት መሳተፉ ይገለጻል።
አሜሪካ ባለፈው ጥር ይህን ቡድን ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ድርጅት በሚል ፈርጃዋለች።