በካርቱም ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው፤ ተመድ አሁን ለድርድር አስቻይ ሁኔታ የለም ብሏል
የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በካርቱም ሰኞ እለት በተካሄደው ጦርነት አንዱ በሌላኛው ላይ ድል ማስመዝገባቸውን እየገለጹ ነው
ከተጀመረ አራት ቀናት በሆነው ጦርነት በካርቱም ውሃ እና መብራት ተቋርጧል
የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በካርቱም ሰኞ እለት ባካሄዱት ጦርነት አንዱ በሌላኛው ላይ ድል ማስመዝገባቸውን እየገለጹ ነው።
ከተጀመረ አራት ቀናት በሆነው ጦርነት በካርቱም ውሃ እና መብራት ተቋርጧል።
ተመድ አሁን ላይ በሁለቱ ለፋለሚ ወገኖች መካከል ድርድር ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ የለም፤ለመደራደር ሁለቱም ፍቃደኝነታቸውን አላሳየም ሲል ገልጿል።
የፈጣን ደራሽ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) ቢያንስ 185 ሰዎችን ገድሎ ከ1,800 በላይ ቆስለዋል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ተናግረዋል።
በሁለት ጀነራሎች የሚመራው የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የስልጣን ሽኩቻ ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንዳትሸጋገር ስጋት ፈጥሯል።
በመዲናዋ ላይ ጭስ ተንጠልጥሏል፣ ነዋሪዎቹም የአየር ድብደባ፣ መድፍ እና የተኩስ ጩኸት መኖሩን ገልጸዋል።
"የሚታገሉት ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው ሰላም እንዲፈጠር ወዲያውኑ ሽምግልና ይፈልጋሉ የሚል ስሜት እየሰጡ አይደለም" ሲል ፔርቴዝ ከካርቱም በቪዲዮሊንክ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
ሁለቱ ወገኖች ለሶስት ሰአት የሚቆይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም ስምምነት መስማማታቸውንም ተናግረዋል።
ከቅዳሜ ጀምሮ በካርቱም እና አጎራባች በሆኑት ኦምዱርማን እና ባህርሪ የሚካሄደው ጦርነት ካለፉት አስርት ዓመታት በላይ የከፋ ነው።
በፖለቲካ ሽግግር ወቅት ስልጣን በነበራቸው ሁለት ወታደራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ሱዳንን የመበታተን አደጋ አለው ተብሏል።
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት እንደቀጠለ ሲሆን ቦታ ከመያዝ አንጻር እርስበእርሱ የሚጋጭ መግለጫ እያወጠለ ይገኛሉ።