“በዓለም ላይ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እንሰራለን”- ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ
መሪዎቹ በኃይል፣ በአየር ንብረትና በግብርና ላይ መምከራቸው ተነግሯል
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ከአሜሪካ፣ ከህንድና እስራኤል መሪዎች ጋር ተወያይተዋል
በዓለም ላይ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ለማድረግ እንደሚሰሩ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመብ ቢን ዛይድ አስታወቁ።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመብ ቢን ዛይድ ከአሜሪካ ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ከህንድ ፐሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲ እና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ ጋር በቪዲዮ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይም የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመብ ቢን ዛይድ፤ ሀገራቸው ከአሜሪካ፣ ከህንድ እና ከእስራኤል ጋር ድንበር ባትጋራም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
የአራትዮሽ ውይይት እና ግንኙነታቸው ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉም ሼክ መሃመድ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም፤ ውይይታቸው በአየር ንብረት፣ በግብርና እና በኃይል ክምችት ላይ ትኩረቱን ያድረገ እንደነበረም አስታውቀዋል።
በጤና አጠባበቅ ላምት እና በጠፈር ምርምር ላይ ለሚሰሩ ስራዎች ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ያነሱት ሼክ መሃመድ ገልጸዋል።
የአረብ ኢሚሬትስ፣ አሜሪካ፣ ህንድ እና እስራኤልን በውስጡ የያዘው “I2U2” ፎረም በፈረንጆቹ በጥቅምት 2021 ላይ ነበር የተመሰረተው።
ፎረሙ ሊመሰረት የቻለው በአራቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተነሳሽነት እንደነበረ ተነግሯል።