”የ97ቱን የቅንጅት ስህተት አንደግመውም” እስክንድር ነጋ
ባልደራስና መኢአድ በምርጫ 2012 በጋራ ስያሜና በጋራ ምልክት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ
ባልደራስና መኢአድ በምርጫ 2012 በጋራ ስያሜና በጋራ ምልክት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ
ባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ቅንጅት መፍጠራቸውን በትናንትው አስታውቀዋለ፡፡
ፓርቲዎቹ በቀጣይ ለሚደረገው የ 2012 ዓ.ም ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆንና ሰብሰብ ማለት ውጤታማ እንደሚያደርግ በመገንዘብ ነው ይህንን ያደረግነው ብለዋል፡፡ ባልደራስ መኢአድ በሚል መጣመራቸውን ያስታወቁት ፡፡
ጥምረቱ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመታል፣ጽንፈኝነትን ለመታገል፣በምርጫ ጊዜ በጋራ ስያሜና በጋራ ምልክት ለመወዳድር፣ለብሔራዊ ጥቅም ለመታልና ሌሎችንም ጉዳዮች ለማሳካት እንሆነ ገልጸዋል፡፡
የመሰረቱት ጥምረት "ባልደራስ መኢአድ" ተብሎ እንደሚጠራም ነው የተገለጸው፡፡
ጥምረቱ ላለመፍረሱ ምን ማስተማመኛ አለ
በ1997 ዓ.ም በነበረው ምርጫ ቅንጅትን የመሰረቱ የፖለቲካ ሃይሎች እስከመጨረሻው አለመዝለቃቸውን ተከትሎ አሁንም ብዙዎች የፓርቲዎችን ጥምረት በጥርጣሬ እንደሚያዩት ይገልጻሉ፡፡ይህ ጥያቄም ዛሬ ጥምረት ለመሰረቱት ፓርቲዎች ቀርቦ ነበር፡፡
የባላደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ይህ ጥምረት ትልቅ ደረጃ የሚደርስ ነው ብለዋል፡፡ በ 1997 ዓ.ም ቅንጅት የደረሰበት ችግር በዚህ ጥምረት ላይ አያጋጥምም ያሉት አቶ እስክንድር ጥምረቱ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንጅ የሚያሳዝነን እንደማይሆን ተስፋ አለንም ብለዋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዘዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በበኩላቸው በጋራ ብዙ ችግሮችን ያየን በመሆኑ ከቀደሙት ብዙ ትምህርት እንወስዳልን ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በሃገሪቱ ያለው የጸጥታ ችግርና አለመረጋጋት እያለ ምርጫ ማድረግ ይቻላል ወይ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ አቶ ማሙሸት ”በርካታ ችግሮች አሉ፣ ነገር ግን መንግስትና ምርጫ ቦርድ ምርጫ ይደረጋል ብለዋል፣ ስለዚህ ለዚህ እኛም እንደ ፓርቲ ዝግጁ ነን›› ብለዋል፡፡
ይሁንና ቀጣዩ ምርጫ ብዙ መሰናክሎች ይበዙበታልም ብለዋል አቶ ማሙሸት፡፡
የዓባይ ጉዳይ
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለውን ግድብ በተመለከተ ከግብጽ በኩል ብዙ ፕሮፖጋናዳዎች እየቀረቡ መሆኑን የገለጹት የፓርቲዎቹ ኃላፊዎች ለብሔራዊ ጥቅም ሁሉም በአንድነት ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡ የዐረብ ሊግ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንደሚያወግዝም ነው ‹‹ባልደራስ መኢአድ›› ያስታወቀው፡፡
የባላደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ዐረብ ሊግ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ የሚወገዝ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ ዐረቦችና ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያቀራርቡን ጉዳዮች አሉ፣ ወዳጅነቱ ነው የሚበጀው፣ ስለዚህ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መግባታቸውን ማቆም አለባቸው›› ብለዋል፡፡