ጆ ባይደን ከቤተመንግስትና ከዋሽንግተን ሲሰናበቱ ምን አሉ?
የተሰናበቱት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቤተመንግስታቸውን እና ዋሽንግተንን ተሰናብተው የግል ህይወታቸውን ለመምራት ወደ ካሊፎርንያ ሲያቀኑ "ከትግል አንርቅም" ሲሉ ተናግረዋል
ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባሰሙት ንግግር በባይደን ጊዜ የነበሩትን ሁሉንም ነገሮች "ሙሉ በሙሉ እና በአጠቃላይ እቀይራለሁ" ብለው ቃል ገብተዋል
የተሰናበቱት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቤተመንግስታቸውን እና ዋሽንግተንን ተሰናብተው የግል ህይወታቸውን ለመምራት ወደ ካሊፎርንያ ሲያቀኑ "ከትግል አንርቅም" ሲሉ ተናግረዋል።
ባይደንን የተኩት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባሰሙት ንግግር በባይደን ጊዜ የነበሩትን ሁሉንም ነገሮች "ሙሉ በሙሉ እና በአጠቃላይ እቀይራለሁ" ብለው ቃል ገብተዋል።
ባይደን ከአራት አመት በፊት ከኦቫል ቢሮ ወይም ኃይትሀውስ የወጡትን ትራምፕን ምርጫ 2024 አሸንፈው በድጋሚ ወደ ቤተመንግስት ሲገቡ ተቀብለዋቸዋል። ትራምፕ በምርጫ 2020 መሸነፋቸውን ስላልተቀበሉ ባይደን በ2021 በዓለ ሲመት ሲፈጽሙ ትራምፕ ተመሳሳይ አቀባበል ሳያደርጉላቸው ቀርተዋል።
ከባለቤታቸው ጂል ጋር ሆነው ትራምፕንና ባለቤታቸውን ሜለኒያን በኃይትሀውስ የተቀበሉት
ባይደን ትራምፕን "እንኳን ወደ ቤትህ መጣህ" ብለዋቸዋል። ከእዚያ በኋላ ታቃራኒ የፖለቲካ ታሪክ ያላቸው ተቀናቃኞቹ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለመሀላ ወደሚፈጽሙበት ካፒቶል አቅንተዋል።
"የቅርቡ ምርጫችን አሳዛኝ የሆነውን ክህደት ሙሉ በሙሉ እና በአጠቃላይ የምንቀለብስበት" ነው ሲሉ ትራምፕ ስለባይደን አስተዳደር ስራ ተናግረዋል። ባይደን ዝም ብለው በፊተኛው ረድፍ ላይ ተቀምጠው ታይተዋል።
ትራምፕ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን በሚያደርጉበት ወቅት የቤተመንግስት ሰራተኞች የባይደን እቃወችን በማስወጣት ተወጥረው ነበር። የቅየራ ስራው የኦቫል ቢኖን በድጋሚ ማደስንም ያካትታል። ጠዋት ባዶ የነበሩትን የቢሮው ግድግዳዎች ከሰአት በአዲስ የትራምፕ ፎቶግራፎች አጊጠው ታይተዋል።
ከትራምፕ በዓለ ሲመት በኋላ አዲሱ ፕሬዝደንት እና ባለቤታቸው ሰራተኞቻቸውን ወደሚሰናበቱበት ወደ አንድሬው ኤየርፓርት የምትወስዳቸው ሄሊኮፕተር ወደቆመችበት ካፒቶል ሸኝተዋቸዋል።
"ከቢሮ እየወጣን ነው፤ ትግሉን እንተውም" ሲሉ ባይደን ለተሰበሰቡት ሰራተኞች ተናግረዋል።
"ወደ ታሪክ የሚገባበትን ጊዜ የመረጠ ፕሬዝደንት የለም፣ ነገርግን አብረው ወደ ታሪክ የሚገቡትን ቡድን ይመርጣሉ፤ በአለም ምርጥ ቡድን ነበረን" ብለዋል ባይደን።
ትራምፕ ቢሮው ከገቡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ አሜሪካ ከአለምጤና ድርጅት፣ ፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እንድትወጣ የሚያደርጉትን ጨምሮ በርካታ ትዕዛዞችን አስተላልፈዋል።