“የአውሮፓ ሕብረት አሁን ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር ዩክሬንን ሙሉ አባል ማድረግ ነው”- የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ዩክሬን፤ ፑቲን “የጦር ወንጀል ፈጽመዋል” ብላለች
ዓለም ሩሲያ የበለጠ እንድትገለል ማድረግ እንደሚገባ ኪቭ ጠይቃለች
አሁን ላይ የአውሮፓ ሕብረት ማድረግ ያለበት ነገር ዩክሬንን ሙሉ አባል ማድረግ እንደሆነ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ።
የሀውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዲምይትሮ ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጹሁፍ የአውሮፓ ሕብረት አሁን ማድረግ ያለበት ኪቭን አባል መድረግ እንደሆነ ገልጸው ይህም ያለመዘግየት መፈጸም እንዳለበት አንስተዋል።
ታሪካዊ ጊዜያት ትልቅ እና ታሪካዊ ውሳኔዎችን እንደሚፈልጉ የገለፁጽ ሚኒስትሩ የሀውጭ ጉዳይ፤ ይህም የሁነቶችን ለውጥ በተገቢው መንገድ ለማስኬድ እንደሚጠቅም ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በካርኪቭ በሚገኘው ሴንትራል ፍሪደም አደባባይ አካባቢ የሚገኙ የመኖሪያ አካባቢ በሩሲያ ሚሳኤሎች ጥቃት እንደተሰነዘረበትም ተናግረዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጦር ወንጅል መፈጸማቸውን የገለጹት የዩክሬኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የንጹሃን ግድያ እንዳለም ገልጸዋል። ዓለም ከዚህ በላይ መስራት እንደሚችልና መስራትም እንዳለበትም ታናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ሩሲያ ላይ ጫና፣ ግፊትና ማግለል እንዲደረግም ዲምይትሮ ኩሌባ ጥሪ አቅርበዋል።
ዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ውስጥ ከገቡ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው ሲሆን ትናንትና ደግሞ የሰላም ንግግር ጀምረዋል። ኪቭ ወረራ እንደተፈጸመባት ስትገልጽ ሞሽኮ ደግሞ ወታደራዊ ተልዕኮ መጀመሯን ገልጻ ነበር።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ አሜሪካ፣ ቤላሩስ ከሩሲያ ጎን ናት በሚል በሚኒስክ ያለውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን ትናንት አስታውቃለች።
ዩክሬንና የሩሲያ ጉዳይ እስከተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የደረሰ ስብሰባ ያስነሳ ሲሆን በዚህም የተባበሩት ዐረብ ኢሚሬቶች፣ ሕንድና ቻይና በሩሲያ እና ዩክሬን ጉዳይ ላይ ተመድ ላቀረበው ሃሳብ ድምጸ ተአቅቦ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ዓለምን ወደት እየወሰዳት ነው የሚሉ ጠያቂዎች እየተበራከቱ ሲሆን፤ ጦርነቱ የዓለምን የፖለቲካና የኦኮኖሚ አሰላለፍ ሊቀይር እንደሚችል እየገመቱ ነው።