ከነገው የመንግስት ምስረታ መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑት የአዲስ አበባ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት መሃመዱ ቡሃሪ በመርሃ ግብሩ ለመገኘት ዛሬ ከአቡጃ ተነስተዋል መባሉ የሚታወስ ነው
በመርሃ ግብሩ ለመታደም የተለያዩ ሃገራት መሪዎችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ወደ ከተማዋ እንደሚመጡ ይጠበቃል
የኢፌዴሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ መዲናዋ እንደሚመጡ የጠቀሰው ፖሊስ እንግዶቹ በአጀብም ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ጠይቋል፡፡
የመንግስት ምስረታው ፕሮግራም በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ ጀምሮ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫዎች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በነገው ዕለት ደግሞ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የመንግስት ምስረታው ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆኑ ግብረኃይሉ አስታውቋል፡-
1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን
19. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
20. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
21. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
22. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
23. ጎርጎሪዮስ አደባባይ