በፈረንሳይ ከተፈጸመው የባቡር ሀዲድ ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው?
ፓሪስን ከሌሎች ከተሞች የሚያስተሳስሩ ፈጣን ባቡር ላይ በተፈጸመ የረቀቀ ጥቃት ትራንስፖርት እንደተስተጓጎለ ነው
አትሌቶችን የጫኑ ሁለት ባቡሮች ባሉበት እንዲቆሙ ተደርገዋል
በፈረንሳይ ከተፈጸመው የባቡር ሀዲድ ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው?
በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው ተወዳጁ የኦሎምፒክ ውድድር ከ100 ዓመት በኋላ ወደ ፓሪስ ተመልሷል፡፡
ዛሬ አመሻሽ በሚጀመረው በዚህ ውድድር ላይ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ከ7 ሺህ 500 በላይ የዓለም አትሌቶችን ጨምሮ ሚሊዮኖች ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ይሁንና በመላው ፈረንሳይ ዛሬ አዳር በባቡር ሀዲዶች ላይ ሆን ተብሎ በተፈጸመ የመሰረተ ልማት ውድመት ምክንያት የባቡር ትራንስፖርት ተቋርጧል፡፡
የሀገሪቱ ባቡር ትራንስፖርት ድርጅት እንዳስታወቀው ሆን ተብሎ በባቡር ሀዲዶቹ ላይ በተፈጸመ ከባድ ጥቃት ምክንያት አገልግሎቱ መቋረጡን ገልጿል፡፡
ይህንን ተከትሎም በመላው ፈረንሳይ ፈጣን ባቡር ትራንስፖርት የተሰረዘ ሲሆን ጉዳዩ በሀገሪቱ ድንጋጤን ፈጥሯል ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት የወንጀሉን ፈጻሚዎች ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆናቸውን ከማሳወቅ ውጪ በይፋ የተጠርጣሪዎችን ማንነት አልያም ስም አላሳወቁም።
አሜሪካ በበኩሏ የባቡር ሀዲዱ ላይ ውድመት ያደረሱት አክራሪዎች አልያም ስርዓት አልበኞች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ አስታውቃለች።
ይህ በዚህ እንዳለ በሁለት ባቡር መስመር ሆነው ወደ ኦሎምፒክ መክፈቻ ፕሮግራም በማምራት ላይ የነበሩ አትሌቶች ጉዟቸውን እንዲያቆሙ የተገደዱ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ብሪታንያ እና ሌሎችም ሀገራት የፈረንሳይ የደህንነት ተቋማት ድጋፍ ከፈለጉ ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ጥቃቱ ዛሬ አመሻሽ በሚደረገው የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ውድድርን ለማስተጓጎል ታስቦ የተፈጸመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡