አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ኬር ስታርመር ማን ናቸው?
ላለፉት 14 ወራት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ሪሺ ሱናክ ስልጣናቸውን አጥተዋል
በብሪታንያ በተካሄደ ጠቅላላ ምርጫ ላለፉት 15 ዓመታት የበላይነት ይዞ የነበረው ወግ አጥባቂ ፓርቲ በሰራተኞች ፓርቲ ብልጫ ተወስዶበታል
አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ኬር ስታርመር ማን ናቸው?
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ሪሺ ሱናክ ከወራት በፊት ምርጫ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ ከሰሞኑ ምርጫ አካሂዳለች።
በዚህ ምርጫ ላይም በኬር ስታርመር የሚመራው የሰራተኞች ፓርቲ ወግ አጥባቂ ፓርቲን በፍጹም የበላይነት አሸንፏል።
የብሪታንያ ህግ አውጪ ምክር ቤት ካለው 650 መቀመጫ 412 መቀመጫዎችን ሲያገኝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ደግሞ 121 ወንበሮችን አግኝቷል።
ይህን ተከትሎም ኬር ስታርመር አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል።
ኬር ስታርመር ማን ናቸው?
ከፈረንጆች 2020 ጀምሮ የሰራተኞች ፓርቲን መምራት የጀመሩ ሲሆን ፓርቲያቸው ያገኘው ድል ከ85 ዓመት በኋላ የመጀመሪያው ናቸው።
የ61 ዓመቱ ስታርመር አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑ ሲሆን ከፓርቲ ፖለቲካ ይልቅ ለሀገር ኢኮኖሚ መረጋጋት ቅድሚያ እንደሚሰጡ አስታውቋል።
የህግ ባለሙያ የሆኑት ስታርመር በተለይም የወንጀል ጉዳዮችን በመመርመር የተዋጣላቸው ባለሙያ ነበሩ ተብሏል።
ከለንደን ከተማ ወጣ ባለችው ሱሬይ በተሰኘችው አነስተኛ ከተማ የተወለዱት ስታርመር እሁለቱም ወላጆቹን በሞት እንዳጡ ተገልጿል።
አባቴን በህይወት እያለ አንድም ቀን እወድሀለሁ ብዬው" አለማወቄ ምንግዜም ይቆጨኛል" የሚሉት ስታርመር ከቤተሰቦቹ ውስጥ ወደ ዩንቨርስቲ በመግባት የመጀመሪያው ሰውም ናቸው።
ለመጀመሪያ ጊዜም በፈረንጆቹ 2015 ላይ የሰራተኞች ፓርቲን ወክሎ የብሪታንያ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆኑ ስታርመር ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ተሾሟል።
የብሪታንያ 58ኛው ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ስታርመር ቪክቶሪያ ስታርመር ከምትባለው ሚስቱ የሁለት ልጆች አባትም ናቸው።