በአፍሪካ እስካሁን 1 ሺ 400 ሰዎች በአዲሱ የፈንጣጣ በሽታ ዝርያ መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
ቫይረሱ የምዕራብ አፍሪካ እና የማዕከላዊ አፍሪካ የተሰኙ ሁለት ዓይነት ዝርያዎች ያሉት መሆኑ ይታወቃል
አዲሱ የፈንጣጣ በሽታ ዝርያ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት መገኘቱን ድርጅቱ አስታውቋል
በአፍሪካ እስካሁን 1 ሺ 400 ሰዎች በአዲሱ የፈንጣጣ በሽታ ዝርያ (ሞንኪ ፖክስ) መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
አዲሱ የፈንጣጣ በሽታ ዝርያ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት መገኘቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
ዝርያው የተገኘባቸው ሃገራት በማዕከለዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በላይቤሪያ፣ በናይጄሪያ፣በኮንጎ ብራዛቪልን እና በሴራሊዮን ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ ቁጥሩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲጻጸር ዝቅተኛ መሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ 4 ሺህ 800 የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ከሞት ጋር የሚታገሉ ህሙማን መኖራቸው ተገለጸ
ቫይረሱ በአፍሪካ ምድር ከተከሰተበት ከ1970ዎቹ ጀምሮ በተሰጋው ደረጃ ወደ አዳዲስ የአፍሪካ ሀገራት ባይስፋፋም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የስርጭት ሁኔታው እያደገ የመምጣት አዝማሚያ ማሳየቱ ይነገራል፡፡
ለዚህም ድርጅቱ ናይጄሪያን እንደማሳያ አድርጎ አቅርባል፡፡ እ.ኤ.አ በ2019 በናይጄሪያ ደቡባዊ ክፍል የታየው ቫይረሱ አሁን ላይ ወደ ሰሜናዊ፣ ምስራቃዊ እና ማእከላዊ የሀገሪቱ ክፍሎች መዛመቱ ሁነኛ ማሳየ ነውም ተብሏል፡፡
ድርጅቱ “የቫይረሱ ስርጭት ለመቆጣጠር አሁንም የጋራ ዝግጁነት አስፈላጊ ነው” ሲልም አሳስቧል፡፡
አሁን ላይ እየተስፋፋ የመጣው ሞንኪ ፖክስ በአፍሪካ ገጠራማና ጥቅጥቅ የደን ይዞታ ባላቸው አካባቢዎች በብዛት እያጋጠመ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ቫይረሱ የምዕራብ እና የማዕከላዊ አፍሪካ የተባሉ ሁለት ዓይነት ዝርያዎች እንዳሉትም ይነገራል፡፡
ለቫይረሱ የመጋለጥ ስጋት እንዳደረባት የገለጸችው ኢትዮጵያ በመግቢያና መውጫ በሮች የቅኝትና ቁጥጥር ስራዎችን እንደምታደርግ መግለጿ ይታወሳል፡፡