ህገመንግስት የመተርጎም ኃላፊነት የተሰጠው አካል ተግባርና አደረጃጀት ምን ይመስላል?
ህገመንግስት የመተርጎም ኃላፊነት የተሰጠው አካል ተግባርና አደረጃጀት ምን ይመስላል?
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያተ የዘንድሮው ምርጫ እንዲራዘም ተወስኖ፣ በዚሁ ጉዳይ “ህገመንግስታዊ ትርጉም” አንዲሰጥ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡ከህገ መንግስት አላማ እና ግቦች እንዲሁም መሰረታዊ መርሆች ጋር ለማስተሳሰር ትርጉም ይሰጥባቸው የተባሉት አንቀጾች፡ አንቀፅ 54/1፣አንቀፅ 58/3 እና አንቀፅ 93 ናቸው። ለአንቀጾቹ ትርጉም የሚሰጠው የ“ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ” ሲሆን ትርጉሙን ካከናወነ በኋላ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፡፡