በወርቅ ቁጠባ ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?
በጊዜ ቆይታ የማይዋዥቅ እና የተረጋጋ ዋጋ ያለው ተደርጎ የሚወሰደው ወርቅ ነው
ምጣኔ ሀብታዊ መዋዠቅ እና አለምአቀፍ አለመረጋጋት ባለበት ዘመን፣ ሰዎች ንብረታቸውን ለማቆየት አስተማማኝ መንገድ ይፈልጋሉ
ምጣኔ ሀብታዊ መዋዠቅ እና አለምአቀፍ አለመረጋጋት ባለበት ዘመን፣ ሰዎች ንብረታቸውን ለማቆየት አስተማማኝ መንገድ ይፈልጋሉ።
በጊዜ ቆይታ የማይዋዥቅ እና የተረጋጋ ዋጋ ያለው ተደርጎ የሚወሰደው ወርቅ ነው።
በወርቅ መቆጠብ አስፈላጊ እየሆነ የመጣው የኑሮ ውድነት የሚቋቋም በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ወርቅ ተመራጭ የሚሆነው ጂኦፖለቲካዊ አደጋዎችን የሚቋቋም እና በታሪክ ሀብት ለማስቀመጥ አይነተኛ ዘዴ ተደርጎ ስለሚወሰድም ነው።
ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በሚኖርበት ጊዜ ሀብትን ጠብቆ ለማቆየት በወርቅ መቆጠብ በጣም አስፈላጊ ይሆናል። ከገንዘቦች በተቃራኒ ወርቅ የመግዛት አቅሙን ለረጅም ጊዜ ጠብቆ ይቆያል።
የቁጠባ ዋጋን እንዳለ ጠብቆ ስለሚያቆይ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችና አገልግሎቶች ዋጋ ቢጨምርም የዋጋ ግሽበትን መቋቋም ይችላል።
የተወሰነ የሀብት መጠንን በወርቅ ማስቀመጥ ሰዎች የመግዛት አቅማቸውን ጠብቀው በማቆየት የዋጋ ንረትን ይቋቋማሉ።
ባለተረጋጋ ወቅት እንደሀብት ማስቀመጫ
ወርቅ ሀብትን ጠብቆ ለማስቀመጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሆኑ የታወቀ ነው። ወርቅ በታሪክ ውስጥ አስተማማኝ መገበያያ ሆኖ ያገለገለ እና አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው መሆኑ ለየት ያደርዋል።
የፋይናንስ አለመረጋጋት በሚያጋጥምበት እና የገንዘብ ዋጋ በሚቀንስበት ጊዜ የወርቅ ዋጋ የሚቀንስ አይሆንም። ወርቅ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ወደ ገንዘብ በቀላሉ መቀየር የሚቻል መሆኑ የወርቅን አስፈላጊነት ያጎላዋል።
ሰዎች በወርቅ በሚቆጥቡበት ጊዜ የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት ቢያጋጥምም፣የተረጋጋ እና ማንቀሳቀስ የሚችሉት ሀብት ይኖራቸዋል ማለት ነው።
የጆኦፖለቲካል አደጋዎችን መከላከል
የጆኦፖለቲካል አደጋዎች በፋይናንስ ገበያ እና በገንዘቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ አላቸው። ነገርግን ወርቅ እንደዚህ አይነት አደጋ ሲኖር መቋቋም ይችላል። የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የምጣኔ ሀብት ቀውስ እና የጂኦፖለቲካል ውጥረት በሚኖርበት ወቅት ወርቅ ተቀማጭ ላይ ችግር አይፈጥርም።
ባለሀብቶች የፖለታካና የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት በሚኖርበት ወቅት፣ ሀብታቸውን ወደ ወርቅ መቀየር ይፈልጋሉ።
በአጠቃላይ ሲታይ ባልተረጋጋ አለም ውስጥ ሀብታቸውን መጠበቅ የሚፈልጉ ሰዎች በወርቅ ማስቀመጥ ይጠቅማቸዋል።ቻይና በኔቶ የሚሰነዘርባትን ትችት በመቃወም መብቷን እንደምትጠብቅ አስጠነቀቀች
ቤጂንግ ቻይና የኔቶ ጥምረትን ጥቅምና ደህንነት ታሰጋለች በማለት የቀረበብኝን ውንጀላ እቃወማለች ብላለች።