ኢኮኖሚ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ
የመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ፕሮጀክቱ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል
የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎትና ለጎርፍ ጉዳትን መከላከያ ፕሮጀክቶች የሚውል ነው
የአለም ባንክ የስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ745 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማፅደቁ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው የገንዘብ ድጋ በኢትዮጵያ ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎትና ለጎርፍ ጉዳትን መከላከያ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።
ከገንዘብ ድጋም 445 ሚሊዮን ዶላር ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተመደበ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
- የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሶስት ፕሮጀክቶች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ
- የዓለም ባንክ ለ2025 የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እቅድ የ500 ሚሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ
የመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ፕሮጀክቱ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን በግጭቱ ተጋላጭ ለሆኑ ስቶች እና ህጻናት ይበልጥ ትኩረት እንደሚሰጥም ታውቋል።
እንዲሁም የገንዘብ ድጋፉ በመላ ኢትዮጵያ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለማዳራስ ያለመ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።
ከገንዘብ ድጋ ቀሪው300 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለጎርፍ ጉዳት መከላከያ ፕሮጀክት የሚለው መሆኑም ተመላክቷል።
ድጋ በአዋሽ፣ በኦሞና በስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ በጎርፍና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት የሚደርስባቸውን ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋል።