ኢትዮጵያውያን ያለ ቪዛ በፓስፖርት ብቻ መግባት የሚችሉባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
47 የዓለም ሀገራት ለኢትዮጵያ ፓስፖርት ያዦች ያለቪዛ እንዲገቡ ይፈቅዳሉ
የኢትዮጵያ ፓስፖርት በተቀባይነት በዓለም 93ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል
የዓለም የጉዞ ሰነድ ተቀባይነትን አስመልክቶ ቁጥራዊ መረጃና ደረጃን የሚያወጣው ሄንሌይ የተሰኘው ፓስፖርት መለኪያ ተቋም የ2024 የሀገራት ፓስፖርት ጥንካሬ ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በመረጃው መሰረት ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ሲንጋፖር፣ ጃፓን እና ስፔን ሀገራት ፓስፖርቶች በጥንካሬያቸው ከዓለም 1ኛ የሚለውን በእኩል የተጋሩ ሲሆን፤ የእነዚህን ሀገራት ፓስፖርቶች የያዙ ሰዎች ወደ 194 ሀገራት ያለምንም ቪዛ መግባት ይችላሉ።
በሪፖርቱ መሰረት የፊንላንድ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ስዊድን ፓስፖርቶች በጥንካሬ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ የእነዚህን ሀገራት ፓስፖርት የያዙ ሰዎች ወደ 193 ሀገራት ያለ ቪዛ መግባት ይችላሉ።
አውስትራሊያ፣ ዴንማርክ፣ አየርላንድስ እና ኔዘርላንድ እኩል ነጥብ በማምጣት 3ኛ ሆነዋል፤ የሀገራቱን ፓስፖርት የያዙ ሰዎች ወደ 192 ሀገራተ ያለ ቪዛ መግባት ይችላሉ።
ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ጠንካራው የተባለ ሲሆን፤ የአገሪቷ ፓስፖርት ያላቸው መንገደኞች ወደ 108 የዓለም አገራት መግባት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ፓስፖርት ጥንካሬ ከዓለም 93ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዘ ሰው ያለ ቪዛ ወደ 47 ሀገራት መጓዝ እንደሚችልም ሄንሌይ የፓስፖርት መለኪያ ተቋም አስታውቋል።
ኢትዮጵያውያን ያለ ቪዛ መግባት የሚችሉባቸው ሀገራትም
ያለ ቪዛ ቀጥታ የሚገባባቸው ሀገራት
ባርባዶስ፣ ቤኒን፣ ቦሊቪያ፣ ኩክ ደሴቶች፣ ዶምኒካ፣ ሃይቲ፣ ኬንያ፣ ላኦስ፣ ማዳካስካር፣ ማላዳቪስ፣ ኑዬ፣ ፕላዩ ደሴቶች፣ ፊሊፒንስ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ሲናጋፖር፣ ስሪላንካ፣ ሴንት ቪንሴንትና ግሬኔድስ፣ ሱሪናሜ፣ ጋምቢያ
በመዳረሻ ቪዛ (ቪዛ ኦን አራይቫል) የሚገባባቸው ሀገራት
ባንግላዴሽ፣ ቡሩንዲ፣ ካምቦዲያ፣ ኬፕ ቭርዴ፣ ኮሞሮስ ደሴቶች፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ጋና፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኢራን፣ ማካዎ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞሪሽስ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒካራጉዋ፣ ናይጄሪያ፣ ሳሞዋ፣ ሲሸልስ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሴንት ሉሺያ፣ ታይላን፣ ቲሞርሌስት፣ ቶጎ፣ ታቩሉ እና ዚምባቡዌ ናቸው።