ቻይና የሩሲያን ሉዓላዊነትና ደህንነትን እንደምትደግፍ አስታውቃለች
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸው ሩሲያን መደገፏት እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ይህንን ያሉት ከሩሲያው ፐሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በትናትናው እለት በስልክ ባድረጉት ውይይት ነው።
በውይይቱ ወቅትም ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸው የሩሲያን ሉዓላዊነት እና ደህንነትን እንደምትደግፍ ማስታወቃቸውን ሲሲቲቪ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ዢ አክለውም ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች በተደቀኑበት በዚህ ወቅት ሁለቱ ሀገራት ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ በሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ያለውን መልካም የእድገት አድንቀዋል።
ቤጂንግ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ፈቃደኛ ነች” ሲሉም ዢ ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማደረግ ከጀመረች ከየካቲት ወር ወዲህ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድፒር ፑቲን ጋ በስልክ ሲነጋገሩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
በቅርቡም ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ያሉት ሩሲያ እና ቻይና ድንበር ተሻጋሪ ድልድይ መክፈታቸው ይታወሰሳል።
የድልድዩ መከፈት ሩሲ በዩክሬን ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት በምእራባውያን የተጣለባን ማእቀብ እንድትቋቋም እና የንግድ እንቅስቃሴዋ እንዲያድግ ይረዳታል ተብሏል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከወራ በፊት የበይነ መረብ ውይይት አድርገው የነበረ ሲሆን፤ በውይይቱም የሩሲያ እና የቻይና ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የትብብር ምሳሌ መሆኑን ፕሬዘዳንት ፑቲን ተናረዋል።
ሩሲያ እና ቻይና የጉርብትና እና ወዳጅነት ስምምነትን ከ20 ዓመት በፊት ተፈራርመው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ይሄንን ስምምነት በአምስት ዓመታት ለማራዘም መስማማታቸው አይዘነጋም።
ቻይና እና ሩሲያ በወታደራዊ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጠፈር ሳይንስ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በሌሎች ሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በመስራት ላይ ናቸው።