የሁቲ አማጺ ቡድን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መትቶ መጣሉን ገለጸ
አማጺ ቡድኑ ሰው አልባ አውሮፕላን መትቶ ሲጥል የአሁኑ ለ15ኛ ጊዜ ነው ተብሏል

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሁቲ አማጺ ቡድን በሽብርተኝነት መፈረጅ አለበት ማለታው ይታወሳል
የሁቲ አማጺ ቡድን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መትቶ መጣሉን ገለጸ፡፡
የየመኑ ሁቲ አማጺ ቡድን ንብረትነቱ የአሜሪካ የሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መካከል አንዱ የሆነው ኤምኪው-9 ውጤታማ የሆኑ ወታደራዊ ተልዕኮዎችን በመፈጸም ይወቃል፡፡
የሁቲ አማጺ ቡድን ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪ እንዳለው ከሆነ የአሜሪካ ድሮን በኤል ሁዴይዳህ ወደብ ጥቃት ለማድረስ በቅኝት ላይ እያለ ተመቷል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቡድኑ ከወራት በፊት ተመሳሳይ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መትቶ መጣሉን የገለጸ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ንብረቱ በሁቲ አማጺ ቡድን መመታቱን በወቅቱ ገልጾም ነበር፡፡
የሁቲ አማጹ ቡድን የአሁኑ ጥቃት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ የአሁኑ ለመጀመሪያው ጊዜ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ጥር ወር ለይ እንዳሉት የየመኑ ሁቲ አማጹ ቡድ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ፍላጎት እንዳላቸው ተናረው ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም የሁቲ አማጹ ቡድን የውጭ ሀገር የሽብርተኝት ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት የአሜሪካ ፖለቲከኞች እንቅስቀሴ ጀምረዋል ተብሏል፡፡
ይህ ቡድን እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖሱ ሂዝቦላህ ጋር የጀመረችውን ጦርነት እንድታቆም ሲያስጠነቅቅ የቆየ ሲሆን በእስራኤል ላይ ተደጋጋሚ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሱ ይታወሳል፡፡
እስራኤል ፣አሜሪካ እና ብሪታንያ በየመን የሁቲ ይዞታዎች ናቸው በተባሉ ቦታዎች ለይ በተደጋጋሚ የአየር ላይ ጥቃቶችን ሲያደርሱ ቆይተዋል፡፡