የየመን አማጺያን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መተው መጣላቸውን ገለጹ
ኤምኪው9 የተሰኘው ይህ ሰው አልባ አውሮፕላን በየመን አየር ክልል ውስጥ ቅኝት ሲያደርግ ነበር ተብሏል
አሜሪካ ለእስራኤል ድጋፍ ለማድረግ በመካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ጦር እና መሳሪያዎች ማስፈሯ ይታወሳል
የየመን አማጺያን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መተው መጣላቸውን ገለጹ፡፡
ሐማስ ያልተጠበቀ ጥቃት በእስራኤል ላይ ማድረሱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት 30ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስራኤል በአየር እና በምድር ላይ ጥቃቷን በጋዛ እያካሄደች ትገኛለች፡፡
የየመን ሁቲ አማጺያን በአረብ ባህረ ሰላጤ ቅኝት ሲያደርግ የነበረን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መተው መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ንብረትነቱ የአሜሪካ የሆነ ኤምኪው-9 የተሰኘ ሰው አልባ አውሮፕላን ለእስራኤል ቅኝት እና መረጃዎችን ሲሰበስብ በአማጺያኑ ተመቶ ወድቋል፡፡
አሜሪካ ኤምኪው-9 የተሰኘው ሰው አልባ አውሮፕላኗ ዓለም አቀፍ የአየር ክልልን ጠብቆ እየበረረ እያለ በየመን ወደብ ተመቶ እንደወደቀባት አረጋግጣለች፡፡
በእስራኤል ጦር የተገደሉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር ከ10 ሺህ ያለፈ ሲሆን በየዕለቱም 150 ህጻናት እየተገደሉ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
የሁቲ አማጺያን በኢራን ይደገፋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሲሆን አሜሪካ ለእስራኤል ድጋፍ ካደረገች ሀማስን እንደሚረዱ እና በዋሸንግተን ላይም ጥቃት እንደሚያደርሱ አስጠንቅቀው ነበር፡፡
እስራኤል ከሀማስ ጋር የጀመረችው ጦርነት አለማብቃቱን ገልጻ በጋዛ መኖሪያ መንደሮች ላይ የአየር እና የመድር ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ ትገኛለች፡፡
አሜሪካንንነ ጨምሮ በርካቶች እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲታወጅ ቢጠይቁም የተቃወመች ሲሆን እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ልካለች፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በእስራኤል ጦር ጥቃት ምክንያት በየዕለቱ 300 ህጻናት በየዕለቱ እንደሚገደሉ ገልጾ ጦርነቱ እንዲቆም አሳስቧል፡፡
ቱርክ፣ አራን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ሌሎችም በርካታ ሀገራት እስራኤል ጦሯን ወደ ጋዛ እንዳትልክ እና የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲያሳስቡ የቡድን ሰባት ሀገራትም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ አውጥቷል፡፡