አዲሱ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሂችልማ ስልጣን ከያዙ ገና ስምንት ቀናቸው ነው
ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ሂችልማ በወታደራዊ አዛዦች ላይ የስልጣን ሹም ሽር አካሂደዋል።
የስልጣን ሹም ሽሩን ያካሄዱት ወታደራዊ አዛዦቹ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ይጥሱ ነበር በሚል መሆኑን የዛምቢያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ፕሬዚዳንቱ የአገሪቱን ብሔራዊ ጦር ዋና አዛዥ ሌተናንት ጀነራል ዊሊያም ሲካዝዌን ከስልጣን አንስተዋል።
በዋና አዛዡ ምትክም ኮማንደር ዴኒስ አልቢዝዊን የአገሪቱ ጦር ሀይሎች ዋና አዛዥ አድርገው መሾማቸው ተገልጿል።
ብርጋዴር ጀነራል ጊዮፍሪ ዚሌን ደግሞ የብሄራዊ ጦር ሀይሎች ምክትል አዛዥ አደርገው ሲሾሙ ብርጋዴር ጀነራል ኮሊንስ ባሪን ደግሞ የአገሪቱ አየር ሀይል ዋና አዛዥ አድርገው እንደሾሙ አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አዲሱ ፕሬዚዳንት የአገሪቱ ፖሊስ አዛዥ፤የብሄራዊ አገልግሎት አዛዥ እና ሌሎች ወታደራዊ መሪዎችን በአዲስ አመራሮች መተካታቸውንም ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በወታደራዊ አመራሮቹ ላይ ሹም ሽር ያካሄዱት በቀድሞው አገዛዝ ዘመን የዛምቢያዊያንን የመናገር፤የመኖር እና ሀብት የማፍራት መብቶችን በፖለቲካዊ አመለካከታቸው ምክንያት ተጋፍተዋል ገለልተኛ አይደሉም በሚል መሆኑን ዚገባዎቹ ጠቁመዋል።
የ59 ዓመቱ ኢኮኖሚስት ሂቺሌማ በዛምቢያ ፕሬዝዳንት ምርጫ ታሪክ ለአምስት ጊዜ ተወዳድረው ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫውን ማሸነፍ ችለዋል።
7 ሚሊዮን ዛምቢያዊያን በተሳተፉበት የዚንድሮው ፕሬዝዳንት ምርጫ ሂችልማ ከ50 በመቶ በላይ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ምርጫውን ማሸነፍ ችለዋል።