በአምስት ዓመት ውስጥ ከ 10 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳካት እንደሚሰሩም ፕሬዝዳንቱ ቃል ገብተዋል
አዲሱ የዛምብያ ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ በስለጣን ዘማናቸው ሙስንናን አጥብቀው ለመታገል ቃል መግባታቸው ተነግሯል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ብሄራዊ ምክር ቤት ባደረጉት የመጀመርያ ንግግራቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ለሚፈጸሙ ወንጀሎችም ምንም ትእግስት አይኖረኝም ብለዋል።
በሁሉም መልኩ በሙስና ላይ “ዜሮ የመቻቻል ፖሊሲ አለን”ም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
“በትግሉ ውስጥ የተቀደሱ ላሞች አይኖሩም” ሲሉ የተደመጡት ፕሬዝዳንቱ ፤ሐቀኛ በመሆን የሚገኙ ጥቅሞችን ከፍ በማድረግ እውነተኞች የሚበረታቱበት ስርአት እንደሚዘረጉም ጠቁሟል።
ሂቺሌማ የምርመራ ክንፍ ኤጀንሲዎችን ለማጠናከር እና የሙስና ጉዳዮችን ለመስማት የሚያስችሉ ልዩ ፍርድ ቤቶችን እንደሚያቋቁሙም ቃል ገብተዋል።
የኮፐር-አምራቿ ሀገር ኢኮኖሚ ለማነቃቀት ቁርጠኛ አመራር እንደሚሰጡም ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል።
በችግር ውስጥ ያለ ግን ደግሞ ደፋርና ቆራጥ እርምጃ የሚጠይቅ ኢኮኖሚ መውረሳቸው ያነሱት ሂቺሌማ፤ እንደ ‹ማዕድን ፣ ግብርና እና ቱሪዝም› ያሉ ቁልፍ ዘርፎችን ለማሳደግ እሰራለሁም ብለዋል።
በሉንጉ ሥር የተጀመረውና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር የሚደረገው የተራቀቀ የድርድር ሂደት እንዲሁም በአምስት ዓመት ውስጥ ከ10 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳካት እሳቸው የሚመሩት መንግስት እንደሚሰራም ሂቺሌማ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ያለው የኑሮ መወደድ እና የስራ አጥነት በምርጫ የተሰተፉ ዛምብያውያን የቀድሞ መሪያቸውን ኢድጋር ሉንጉን ድምጽ በመንፈግ ሂቺሌማ እንደሚርጡ ካደረጓቸው ምክንያቶች እንደሆኑ ይታወቃል።
የሂቺሌማ በምርጫ ማሸነፍ በእፍሪካ አህጉር ተቋዋሚዎች አሸንፈው በዴሞክራሲዊ መንገድ በትረ ስልጣን መጨበጥ እንደሚችሉ መሰረት የጣለ አብነታዊ ሽግግር ነው ተብሎለታል።