በሩሲያ ሰሞንኛ ጥቃት 30 በመቶ የዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች መውደማቸውን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ገለጹ
ወታደራዊ ተንታኞች፤ የክሬምሊን እርምጃ ሞስኮ በጦር ሜዳ ላይ ለደረሰው ኪሳራ የሰጠችውን ምላሽ ነው ብለውታል
ዘለንስኪ፤ ጥቃቱ ከፑቲን አገዛዝ ጋር “ለመደራደር የሚስችል ምንም እድል እንደሌለ” የሚያመላክት ነው ብለዋል
ሩሲያ በሰነዘረችው ጥቃት በሳምንት ውስጥ 30 በመቶ የዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን መውደማቸው የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ገለጹ።
ሩሲያ ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች የወሰደችውን በድሮኖች የታገዘ የእርምጃን ተከትሎ በሀገሪቱ የመብራት መቆራረጥና የውሃ አቅርቦት መቆራረጥ እንዳስከተለ ይነገራል።
ቢዘህም በኪቭ፣ በምስራቅ ካርኪቭ፣ በደቡብ እበዲኒፕሮ፣ ዞይቶሚር እና ማይኮላይቭ ግዛቶች የሚገኙ ሆስፒታሎች በመጠባበቂያ ጄነሬተሮች እየሰሩ መሆናቸውን ሮይተርስ የግዛቶቹን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የተስፋ መቁረጥ ጥቃት ሲሉ በገለጹውትና ሰኞ እለት በኪቭ ላይ የተሰነዘረው የድሮኖች የቦምብ ጥቃት በርካታ ከተማዋ የመኖሪያ ህንጻዎች ከማውደም በዘለለ አምስት ሰዎችን ገድለዋል።
ፕሬዝዳንቱ፤ የኢነርጂ መሰረተ ልማትን ተደጋጋሚ ኢላማ ያደረገውን የሩሲያ እርምጃ “የሽብር ጥቃት” ሲሉም ገልጸውታል።
"ከጥቅምት 10 ጀምሮ 30 በመቶው የዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ወድመዋል፤ ይህም በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የኃል መቆራረጥ እንዲፈጠር አድርጓል" ሲሉም ተናግረዋል ዘለንስኪ በትዊትር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት።
ጥቃቱ “ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገዛዝ ጋር ለመደራደር የሚስችል ምንም እድል የለም” እንደማለት ነውም ብለዋል።
ወታደራዊ ተንታኞች በበኩላቸው የወቅቱ የክሬምሊን ባለስልጣናት እርምጃ ሞስኮ በጦር ሜዳ ላይ ለደረሰው ኪሳራ የሰጠችውን ምላሽ ይመስላል ሲሉ ገልጸውታል።
ሩሲያ የኢራን እንደሆኑ በሚነገርላቸው ድሮኖች በመታገዝ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ላይ መሆኗ ይታወቃል።
የአሁን ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ሚሳዔሎች ድብደባ የጦርነቱ መጀመሪያ አከባቢ ሞስኮ ኪቭን ለመቆጣጠር ታደርገው የነበረ መጠነ ሰፊ ጥቃት አይነት ነው ተብሏል።
በዚህም ሩሲያ የኢራን ድሮኖችን እየተጠቀመች ነው የምትለው ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት በቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕከቀብ እንዲጥል በመወትወት ላይ ናት።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሪ ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት "የአውሮፓ ህብረት ለሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማቅረብ በኢራን ላይ ማዕቀብ ሊጥል ይገባል” ብለዋል።